Logo
FastMereja
ኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች ኢንደስትሪ ዘመናዊ የበር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ገንብቶ በመጨረስ አስመረቀ።
#fastmereja - በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥር የሚገኘው ኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግል ማህበር በገላን ከተማ በአይነቱ ለየት ያለ እጅግ ዘመናዊ የበር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ገንብቶ በማጠናቀቅ በዛሬ ዕለት የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮች በተገኙበት አስመርቋል፡፡

ይህ የብረት በር ፋብርካ ከመደበኛ ምርት ስራ ጎን ለጎን ሜዛኒኑን ጨምሮ በ8,400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሙሉ የብረት ስትራክቸር ስራ በራስ አቅም የተሰራ ሲሆን ግንባታዉም በ7 ወራት ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ለቴስቲንግና ኮሚሽንግ ስራ ዝግጁ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፋብርካዉ በቀን ከ300 በሮች በላይ የማምረት አቅም ያለዉ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ከቁልፍ ጋር ከተያያዙት አክሰሰሪዎች ዉጭ በሀገር ዉስጥ ሙሉ እሴት ተጨምሮበት የሚመረት እንደሆነ ተገልጾ በተጨማሪ ፋብሪካው የውጭ ምንዛሬን በማዳን ትልቅ አስተዋጽኦ ከማበርከት አልፎ ለአካባቢው ማህበረሰብም ተጨማሪ የሥራ እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ፋብርካዉ በአሁኑ ጊዜ ከ150 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢዉ ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የብረት በር ፋብሪካው በርካታ መለያዎች አሉት ከነዚህም የቀለም ቅቡ አለማችን በደረሰበት ከፍተኛ ቴክኖሎ* (powder coating and water base painting) በምንም መልኩ በዝገት እንዳይበላሹ ተደርጎ የሚሰሩ በመሆናቸዉ ለበሮቹ ተጨማሪ ውበት እንዲጎናፀፉ ያደረጉ መሆናቸዉ፣ ዘመናዊ እና ውብ የብረት በሮች ሆኖ የእንጨት ባህሪ ያላቸዉ መሆናቸዉ፣ ድምፅ የማያስተጋቡ (Sound proof) ነፍሳት እና ተባዮችን የማያሳልፉ መሆናቸዉ፣ ከስድስት እስከ አስር ድረስ የሚደርስ የቁልፍ ተወርዋሪ ያላቸዉ መሆናቸዉ፣ በደንበኞች ትዕዛዝ የሚገጠሙ ቁልፎች ያሉት በተለይ የስማርት ቁልፉ በአሻራ፣ በፓስወርድ፣ በካርድ መክፈትና መቆለፍ የሚያስችል አማራጮች ያለው መሆኑ፣ በተጨማሪ ከዉስጥ ወደ ውጪ የሚያሳይ ካሜራ፣ ሌንስ እና መጥሪያ ደውል የተገጠመላቸው መሆኑ፣ ከ30 በላይ አማራጭ የበር Design እንዲሁም ከ 20 በላይ የቀለም ምርጫዎች ያለዉ ከአከባቢ ጋር ተስማሚ እና ምንም ዓይነት ተፅዕኖ የመያሳድር የአመራረት ሂደት የሚከተል መሆኑ፤ ለ3 ሰአት ያክል የእሳት አደጋን መቋቋም የሚችሉ (Heat resistant & Fire proof) እንዲሁም የትኛውም አይነት እርጥበት የማያበላሻቸው (water proof) መሆናቸዉ ልዩ ያደርጋቸዋል ተብሏል።
#ቢዝነስ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.