Logo
Getu Temesgen

ዩቶፕያ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ
#ethiopia | ዩቶፕያ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የኤሌክትሪክ ሜትር ታክሲ መተግበሪያ ማስጀመሪያ እና የኤሌክትሪክ መኪና እቁብ የማውጣት ስነ፟ስርአት እና የማስረከብ ፕሮግራም አከናወነ ::

ዩቶፕያ ቴክኖሎጂ ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ፣ አርቲስቶች ፣የሚዲያ አካላት እና ደንበኞች በተገኙበት ዮቶፕያ ኢ፟ታክሲ የተሰኘ መተግበሪያ ማስጀመሪያ እና የኤሌክትሪክ መኪና እቁብ አወጣጥ ፕሮግራም በእስካይላይት ሆቴል አከናወነ፡፡

መርሀግብሩ በአቶ ሰላምይሁን አደፍርስ የኢኖቬሽኝ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፟ የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፤ አቶ አላምረው ጌጡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚ/ር ፟ የክቡር ሚኒሲቴሩ ከፍተኛ አማካሪ እንዲሁም የዩቶፕያ ቴክኖሎጂ ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዶኒክ ወርቁ የመክፈቻ ንግግር በይፋ ተከፍቷል፡፡

አቶ አዶኒክ ወርቁ እንደገልጹት “ድርጅታችን ላለፉት 5 አመታት ሲሰራበት የቆየውን በኢትዮጰያ ፈርቀዳጅ የሆነውን እና ለአካባቢ ንብረት ተስማሚ እንዲሁም ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምነዛሪ የሚያስቀር ዩቶፕያ ግሪን ሞቢሊቲ ኢኒሼቲቭ እየተገበረ ሲሆን በውስጡ “ዩቶፕያ አውቶሞቲቭ” ፣ “ዩቶፕያ ኢ፟ ታክሲ” ፣ “ዩቶፕያ ግሪን ፈንድ” እና “ዩቶፕያ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ እስቴሽን” ፕሮጀክቶች ያካተተ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሀገራችን ለምትከተለው አረንጓዴ-መር ዲጂታል ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋዖ የሚያበረክት ፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፖሮጀክት እንደ ኢምፖርት ሰብስቲትዩት ለመጠቀም እና የኢነርጂ ፍላጎታችንን አካባቢ በካይ ከሆነው ነዳጅ በዋጋ ዝቅተኛ ታዳሽ ኤልክትሪክ ሀይል ለመቀየር ትልቅ እድል ይፈጥራል እንዲሁም ለነዳጅ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል፡፡በተጨማሪም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻግር ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ይቀርፋል” ብለዋል ፡፡

በመክፈቻ ንግግሩ የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ “በዚህ ወጣትነት እድሜ እንደዚህ ትልልቅ ሀላፊነት ወስደው እንደዚህ አይነት ኢኒሼቲቭ አዳዲስ ነገር ለማስተዋወቅ የሚጥሩ እንደ አቶ አዶኒክ ወርቁ ያሉ መስራቾችን ለማመስገን እዋዳለሁ” ብለዋል ፡፡

እንዲሁም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚ/ር ፟ የክቡር ሚኒሲቴሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አላምረው ጌጡ “እንደዚህ አይነት ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅሙ ኢኒሼቲቮች ሊበረታቱ ይገባቸዋል” ያሉ ሲሆን “ሀገራችን የምትከተለውን ግሪንመር ዲጂታል ኢኮኖሚ እና ሰስቴነብል ትራንስፖርት እስትራቴጂ ከማገዝ እኳያ ከፍተኛ አስተዋጾ ይበረክታል፡፡ እኛም እስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር እንደምናደርግ በሚኒቴር መ/ቤቱ ስም ቃል እገባለሁ” ብለዋል ፡፡

በኢትዮጰያ የመጀመሪያ የሆነውን በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ እና ለአካባቢ ምቹ የሆኑ የኢምሽን እስታንዳርዱን የሚያሟሉ ተሽከርካሪዎችን የሚያካትት ዮቶፕያ ኢ፟ታክሲ የተሰኘ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ እና ላለፉት 5 አመታት ጥናት ሲያካሄድበት የቆየውን እና ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ በተጠበቀ የዲጂታል መተግበሪያ የሚተዳደርበትን ዳይናሚክ ሲስተም ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ባሉ ባለሙያዎች ትብብር መዘጋጀቱ በፕሮግራሙ ተገልጻል፡፡

መተግበሪያው ወደ ስራ ሲገባ በከተማው የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር የሚቀርፍ ሲሆን “ዩቶፕያ ኢ፟ ታክሲ”- ስር የሚካተቱ መኪናዎች በታዳሽ ሃይል የሚሰሩ እና ከአካባቢ ብክለት ነጻ ሲሆኑ ለነዳጅ የሚወጣውን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚቀንስ አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ያለመ ነው ፡፡

ሲስተሙ ካካተታቸው በርካታ አዳዲስ አማራጮች አንዱ የሆነው የሜትር ታክሲ በጋራ መጋራት (Ride Sharing system) ሲሆን የጉዞውን ዋጋ በ4 እጥፍ የሚቀንስ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከደህንነት አንጻር ጉዞላይ ማንኛው ችግር ቢፈጠር በቀጥታ ሪፖርት ማድረግ የሚቻልበት አማራጭ በመተግበሪያው ተካቷል፡፡

ደንበኞች ከመተግበሪያው ሳይወጡ ክፍያዎችን ዲጂታሊ ለማከናወን ይረዳችው ዘንድ ከሲቢኢ ብር እና ቴሌ ብር ጋር የሲስተም የማስተሳሰር ስራ (System Integration) እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጻል ፡፡

የዩቶፕያ ኢ-ታክሲ መተግበሪያ ሲስተም በኢትዮፕያ አእምሮአዊ ጽ/ቤት ያስመዘገበ እና የኮፒ ራይት ሰርተፍኬት የወሰደ ሲሆን ተጨማሪ የኦፕሬሽን ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ከፊታችን መስከረም ወር መባቻ ጀምሮ አግልግሎቱን በይፋ እንደሚጀምር ተገልጻል፡፡

ከ6 ወር በፊት ወደስራ በገባው “ዩቶፕያ ግሪን ፈንድ” ኢንተግሬትድ የኤሌክትሪክ የመኪና ፍይናንሲንግ ሲስተም በ5 አመት ውስጥ 5,000 ደንበኞችን የኤሌክትሪክ የመኪና ባለቤት ለማድረግ ያቀደ ሲሆን እስካሁን 1,650 አባላት www.ugmfund.com ሲስተም ላይ የተመዘገቡ ሲሆን ቅድመ ሁኔታዎችን ላሟሉ በርካታ ደንበኞች 3ኛ ዙር የመኪና ማስረከብ ፕሮግራም በቅርቡ ማከናወኑ ተገልጻል፡፡

በዝግጅቱ ሁለተኛ መርሀግብር የዮቶፕያ ግሪን ፈንድ ሲስተምን በመጠቀም ላለፉት 4 ወራት ለመኪና እቁብ ሲቆጥቡ ለነበሩ ደንበኞች የመኪና እቁብ እጣ እወጣጥ ስነስርአቱ ሂደት ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ በተጠበቀ የዲጂታል መተግበሪያ ተጋባዥ እንግዶች የሚዲያ አካላት እና ታዛቢዎች በተገኙብት በይፋ ተከናውኗል፡፡

የመጀመሪያ የመኪና እቁብ እጣ ለአቶ ሙሉጌታ ዋለልኝ የወጣሲሆን አቶ ሙሉጌታ ዋለልኝ እንደገለጹት “ልጄ እድል ከእኛ ጋር ነው ሂድ ይቀናሀል ብሎኝ ነበር ! ይሄው እግዛብሄር ይመስገን 120,000 ብር ብቻ አውጥቼ በአራት ወር ውስጥ የመኪና ባለቤት ሆኛለሁ” ብለዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዶኒክ ወርቁ “ እኛም በጣም ደስተኛ ነን ለረጅም ጊዜ ስንስራበት የቆየነውና ለህዝብ እና ሀገር ይጠቅማል ብለን ያመነጨነው ሀሳብ ወደ መሬት ወርዶ በዝቅተኛ ክፍያ ማለትም የመኪናውን 5% የማይሞላ ወጪ አውጥቶ ደንበኛችን የኤሌክትሪክ ሜኪና ባለቤት በማድረጋችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል ወደፊትም ከዚህ በበለጠ እንቀጥልበታለን” ብለዋል፡፡

በመኪና ቁልፍ እርክክብ ፕሮግራሙ የተሳተፉት የድርጅቱ አምባሳደር የሆኑት እርቲስት እንግዳሰው ሀብቴ “ድርጅቱ ቃል በገባው መሰረት መኪናዎቹን ለደንበኞቹ በማስረከቡ ምስጋናዬን ላቅርብ እወዳለሁ” በማለት ገልጸዋል ፡፡

በዝግጅቱ የዝንድሮ የኢትዮጵያ ቲክቶክ አዋርድ ተሽላሚ የሚሰጥ የኤሌክትሪክ መኪና በዩቶፕያ ቴክኖሎጂ የተበረክተ ሲሆን የዝግጅቱ ተዋካይ የመኪና ቀልፍ ተረክበዋል ፡፡
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.