ግድብ እውን ሆኗል‼️
ይድረስ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ!
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሰላም መጠናቀቁን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።
ለዘመናት የቆየው የትውልድ ህልም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ውሳኔና አንድነት ውጤት የሆነው ይህ ታላቅ ፕሮጀክት፣ አሁን በታሪክ ማህደር ውስጥ ስሙን አስፍሯል።
ይህ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት ብቻ አይደለም። የብዙሃን ኢትዮጵያውያንን ላብ፣ ደም እና ህይወት ዋጋ የተቀመጠበት፣ በጋራ መቆም እና መቻል የሚለውን መርህ ያስመሰከረ የድል አድራጊነት ማሳያ ነው።
በቅርቡ ከሀገራችን ወዳጆች ጋር በመሆን በደማቅ ስነ-ስርዓት የሚመረቅ ሲሆን፣ የግድቡ ግንባታ ማሽነሪዎች ደግሞ ወደ አዲስ የአባይ ፕሮጀክት እየተጓዙ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ይህ የህዳሴው ዘመን የአርበኝነት ታሪክ፣ ለመጪው ትውልድ ትልቅ ትምህርት እና የኩራት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ታሪካዊ ክስተት ነው።
Seledadotio

9 months ago