በጸሃይና በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ መኪናዎች ወደ ገቢያ እየገቡ ነው ተባለ
የዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአካባቢ ጥበቃ ጥምረት፣ ከፀሃይ ብርሃን ኃይል የሚያመነጩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV) በስፋት እየተስፋፉ ነው ተብሏል።
ይህ አዲስ የአኗኗር ዘይቤ፣ የትራንስፖርት እና የኢነርጂ ፍላጎቶችን ለማሟላት አዲስ አቅጣጫ እየጠቆመ ነው ተብሏል።
በተለይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን ከቤቶች የሶላር ፓናል ስርዓት ጋር ማገናኘት፣ አጠቃላይ የኢነርጂ ፍጆታን ለመቀነስ እና ከቅሪተ አካል ነዳጆች ነፃ የሆነ ኑሮን ለማስቻል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ተብሏል። ይህ አሰራር የመጨረሻው አረንጓዴ ህልም ተብሎ እየተጠራ ሲሆን፣ በርካታ ጥቅሞችን ይዞ ይመጣል ነው የተባለው።
የኤሌክትሪክ መኪናውን በቤታችን ከሚገኘው የፀሃይ ኃይል በመሙላት ነዳጅ ለማግኘት የሚያወጣውን ወጪ ሙሉ ለሙሉ ያስቀራል። ይህ ደግሞ በነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ያስወግዳል ተብሏል።
የራሳችን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ ከብሄራዊ የኃይል ፍርግርግ (grid) ነጻ ያደርጋል የተባለ ሲሆን በአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ አይጎዱምም ተብሏል።
የኤሌክትሪክ መኪናዎች ምንም አይነት ልቀት ስለሌላቸው እና የኃይል ምንጫቸውም ታዳሽ ስለሆነ፣ ለአካባቢ መበከል አስተዋፅኦ የላቸውም የተባለ ሲሆን ይህ አካሄድ የካርበን አሻራን ወደ ዜሮ በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ይረዳል ነው የተባለው።
ሶላር ሃይልን ለኤሌክትሪክ መኪና መጠቀም ከነዳጅ እጅግ በጣም ያነሰ ወጪ አለው የተባለ ሲሆን የኤሌክትሪክ መኪናዎች የዘይት ለውጥ ወይም የሞተር ጥገና ስለማያስፈልጋቸው የጥገና ወጪያቸው አነስተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህ አሰራር ወደፊት እየሰፋ የሚሄድ ሲሆን፣ እንደ የባትሪ ማከማቻ (ለምሳሌ Tesla Powerwall) ያሉ ቴክኖሎጂዎች እየተጨመሩበት ነው፤ ይህም በሌሊትም ቢሆን መኪናውን በሶላር ሃይል ቻርጅ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።
በተጨማሪም መኪናን እንደ የኃይል ማጠራቀሚያ በመጠቀም ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውልበት "vehicle-to-grid" ቴክኖሎጂም እየተስፋፋ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ አብዮት የኃይል አጠቃቀማችንን እና የትራንስፖርት ባህላችንን ወደፊት የሚቀይር አዲስ ምዕራፍ ነው ተብሏል። ይህ ዘመናዊ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ አካሄድ፣ ለወደፊቷ ምድር ዘላቂ መፍትሄዎችን እየጠቆመ መሆኑም ተመላክቷል።
Seledadotio

1 year ago