ማንችስተር ዩናይትዶች እና ሴኒ ላመንስን
✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
በማንችስተር ዩናይትዶችየቤልጅሙን አንቱዎርፕ ክለብ ግብ ጠባቂውን ሴኒ ላመንስን ለማስፈረም እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል፤ ከተጫዋቹ ጋር ግል ጥቅማጥቅም ጉዳይ መስማማታቸውንም በርካታ የዜና ምንጮች እየዘገቡ ነው
****
የባሎን ዶር አሸናፊው የማንችስተር ሲቲው አማካይ ሮድሪና ፊል ፎደን ከጉዳት መልስ ለነገው የማንችስተር ሲቲና ቶተንሃም ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫው ተናግሯል። ፔፕ ስለሁለቱም ተጫዋቾች ሲናገር " ለወልቭሱ ጨዋታ 90 ደቂቃ ባይሆንም ለመጫወት ዝግጁ ነበሩ፤ ነገር ግን አሁን ላይ ለነገው ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ናቸው" በማለት ሁለቱም የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች በኢትሀዱ ጨዋታ ሊሰለፉ እንደሚችሉ አረጋግጧል።
***
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫው ስለቪክቶር ጊዮኬሬሽ በሰጠው አስተያየት ቪክቶር እጅግ በጣም ጉጉት ላይ ነው፤ሳምንቱን በሙሉ ጠንንሮ ልምምድ ሲሰራ ነበር፤በጣም ጥሩ ቦታ ላይ ነው የሚመስለው። በማለት አጥቂው ያለበትን ሁኔታ ገልጿል።
ስለተጋጣሚያቸው ሊድስ ዩናይትድ ደግሞ እጅጉን መደነቁን ገልጿል። በቅድመ-ውድድር ወቅት ያደረጉትን፣ ሰኞ ላይ ከኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ፣ባለፈው አመት ላደረጉት ሁሉ አሰልጣኛቸውን ዳንኤል ፋርከን ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፆ የነገውን ጨዋታ በእርግጠኛነት ከባድ ግጥሚያ ሊያደርጉባቸው እንደሚችሉ ተናግሯል።
***
በመጀመሪያው ጨዋታቸው በግዙፉ ኦልድትራፎርድ በአርሰናል የአንድ ለዜሮ ሽንፈት የደረሰባቸው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እሁድ ከፉልሃም ጋር በክራቫን ኮቴጅ የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለራስመስ ሆይሉንድ "ራስመስ ከቡድኑ ውጪ መደረጉን ያስተናገደው በፕሮፌሽናል መንገድ ነው ነገር ግን አጠቃላይ ነገሩን ለመናገር የዝውውር መስኮቱ እስኪዘጋ መጠበቅ አለብን" ብሏል።
ሩበን አሞሪም አክሎም ስለፉልሃሙ ጨዋታ የሚከተለውን ተናግሯል
"ከፉልሃም ጋር መጫወት በጣም ከባድ ነው። ግልፅ የሆነ የአጨዋወት መለያ አላቸው አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫም ትልቅ ብልህ ነው በማለት ማርኮ ሲልቫንና ቡድናቸውን አድንቋል፤ ፉልሃሞች ሊጉን በሚገባ የተረዱና ልምድ ያላቸው በሆኑ ጨዋታው ከባድ ነው ነገር ግን ደግሞ ሁሉም የሊግ ጨዋታዎች ከባድ ናቸዉ ብሏል።
አያይዞም በባለፈው ጨዋታ ጥሩ ነገሮች ነበሩን ጠንካራ ነገራችን የበለጠ እናጠናክራለን የታዩብን ክፍተቶች ላይና የጎደሉን ነገሮች ላይ ደሞ ጠንክረን እንሰራለን። ተጋጣሚዎቻችንን በሚገባ አጥንተን ከቆሙ ኳሶች የሚመጣን ጎል እንከላከላለን ይህን የምናደርገው ለሁሉም ተጋጣሚዎቻችን ነው " ብለዋል።

12 months ago