ሙሉጌታ ገሠሠ አብርሃ (1951-2017)
ሬዲዮ ፋና 1987 ክረምት፣
#ethiopia | ሰፊ እና የስብሰባ ጠረጴዛው የክፍሉን ሶስት አራተኛ ቦታ በያየዘው ቢሮው ውስጥ ከሙለር ጋር ፊት ለፊት ተቀምጠናል፤ ከጀርባው የተኮፈሰው ትልቅ የግሩንዲንግ ሬዲዮ ያለህበትን ቦታ ስሜት ያደምቅልሃል፤ የሬዲዮ ፋና መሥራች ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ውስጥ ነን፤ ጣቢያው እንደ ፋና ገና ወራት ያስቆጠረ ዕድሜ ላይ ነው፤ ወደ ሌላው የሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን ኢንተርፕራይዝ የተዘዋወርኩበት ቀን ነው፤ ፋና መግባት ደብሮኛል፤ የፖለቲካ ፓርቲ ጣቢያ እንደሆነ እና ዘገባዎቹም የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ስለሆኑ ራሴን ያዘጋጀሁለት ዘርፍ አልነበረም። “ብቻ ልየው” እያልኩ ነው ግቢው ውስጥ የተገኘሁት፤ ሙሉጌታን በተለያዩ አጋጣሚዎች ቀደም ሲል አውቀዋለሁ፤ ዝናው የሚቀድመው እና ስታገኘውም ዝናውን የሚመጥን ስነልቦናው ይቀበልሃል።
ወጣትነት ደፋር ያደርጋል፤ ስለቅጥር ሁኔታ ተነጋገርን እና ከበፊቱ መስሪያቤት ደመወዜ ላይ 50 ብር ተጨምሮልኝ እንደምቀጠር ነገረኝ፤ (ዛሬ ላይ ጌጡ ተመስገን ለለማኝ የሚሰጠው ገንዘብ ማለት ነው፤) ገንዘቡ ብዙም አላሳሰበኝም፤ የኔ ሃሳብ ሌላ ነው፤ “የህወሓት ጣቢያ ውስጥ ገብቼ አንደበቴን ለድርጅቱ” የማበደሩ ጉዳይ ምቾት አልሰጠኝም፤ አድናቆቶችን ከቸረኝ በኋላ ሙለር የኔን መልስ ጠበቀ።
“የፈለከውን ነገር እዘዘኝ፣ ነገር ግን ፕሮግራም ሥራ አትበለኝ፤” አልኩት፤ “ከፈለገ አይቀበለኝ፤” ብዬ ወስኛለሁ፤ ሙሉጌታ ምንም አላለኝም፤ ፈገግ አለና “ችግር የለም፤” አለኝ፤ ትልቅ ሸክም ከራሴ ላይ ወረደልኝ፤ ሙሉጌታ ዲሞክራት ነው፤ አልኩ፤ በዚህ መልክ የተጀመረው ግንኙነታችን ሶስት አሰርትን በደፈነበት አመት ሙለር ተለየን።
የመታሰቢያውን ቀን ስናከብር ብዙ ነገሮቹን አስታወስን፤ ሙለር ገዝፎ መጣ፤ ምነው ቆሞ ባየው የሚያሰኝ የመታሰቢያ ዝግጅት ተደረገለት፤ የድሮ ባልደረቦቻችን ሃሳባቸውን፣ ትዝታቸውን፣ ለሙለር ያላቸውን ፍቅር፣ ክብር እና አድናቆት ተራ በተራ ገለጹ፤ ሙሌ የፍቅር ሰው፣ ሙሌ የአመራር ሰው፣ ሙሌ የሙያ አባት፣ ሙሌ ትሁቱ እና ሙሌ የተጽዕኖ ሰው፤ ብዙ ተባለለት። አንዱም ግነት የሌለው አገላለጽ ነበር።
ሙሌ ሥልጣን የለውም፤ ባለሃብትም አይደለም፤ ሙሌ የመድረክ ሰው አይደለም፤ ወይም በመንፈስ የተቀባ የእምነት አስተማሪ ወይም ስመገናና ዑስታዝም አይደለም፤ ሙሌ ሴሌብሪቲም አይደለም። ግን እነዚህን ሁሉ ሳይሆን ከነዚህ ተርታ የሚያሰልፍ የፍቅር አቅም አለው፤ በርግጥ ሙሌ ከሚዲያው መድረክ ከወጣ እና ባይተዋርነትን ከመረጠ እንኳን 24 አመታት ቢሆኑትም በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ ያስቀመጠው የፍቅር ዲፖዚት መታሰቢያው ላይ ተገኝተን እሱን ሸኝተን ስብዕናውን እንድንዘክር እና እንድናስተላልፍ ግድ ብሎናል፤ ሙሉጌታ በአንድ ሰውነት ውስጥ በርካታ ጸጋዎችን የደረበ ሰው ነው፤ ፍቅር፣ ወንድምነት፣ አባትነት፣ ጓደኛነት፣ ትህትና፣ ጽናት፣ ክብር እና ሞገስ የተላበሰ ሰው፤ እነዚህ ሁሉ ንጥረባሕርያትን አንድ ሰው ውስጥ ማግኘት ከባድ ነው፤ ግን ሙሌ ይዟቸው ሄደ፤ ስብዕናን ይጋሩታል እንጂ አይወርሱትም።
የመታሰቢያው ዝግጅት እውነተኛነት እና ድምቀት ግን ከታወቁ እና በዘርፋቸው ቁንጮ ላይ ሆነው፣ ህይወታቸው ካለፉ ጉምቱዎች ጋር የሚስተካከል ክብር ያለው መሆኑ ያስገርማል፤ መልሱ ሙሌ እውነተኛ እና የፍቅር ሰው ስለነበረ ነው፤ ዝግጅቱም እንደሙለር እውነተኛ ነበር፤ በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ምንም ግብዝ ነገር ፈልገው የመጡ አይደሉም፤ ድሮ የመራቸው፣ ያሳደጋቸው፣ ያበቃቸው እና የፍቅር ውርስ የተወላቸው ባልደረቦቹ እና ወዳጆቹ ናቸው፤ ተራ በተራ እየተነሱ የተናገሩለትም በአንድም በሌላም ሙለር በህይወት የነካቸው ሰዎች ናቸው፤ እውነተኛ ስሜታቸውን ተናግረዋል፤ ነገር ግን ጊዜ ገደባቸው እና ሙለርን በፈለጉት እና በልኩ አልገለጹትም፤ ሙለር የሚገርም ስብዕና የተላበሰ ሰው ነው።
በረሃ (ትግል ላይ) በነበረበት ወቅት ሙለር ለየት ያለ ስብዕና እንደነበረው ይነገርልታል፤ ስብሰባዎች ላይ አይናገርም፤ የድርጅቱ አንጋፋዎች መጥተው እንኳን ሲያወዩዋቸው ሙሌ ትንፍሽ ሳይል ስብሰባው ያልቃል፤ በደርግ አጋርፋ እርሻ ኮሌጅ ተመርቆ የሰራበትን ዘመን ህወሓቶች በጥርጣሬ የሚያዩት ክፍለ-ህይወቱ ነው፤ ህወሓቶች መንደር ውስጥ ሙሉ ታማኝ ለመሆን፣ ወጥ-አባል (ከልጅነት ጀምሮ እና ከሌላ ፖለቲካዊ አካል ጋር ሳይነካካ የመጣ) መሆን አለብህ፤ አለበለዚያ እያንዳንዷ ስህተት ከኋላ ታሪክህ ጋር ተያይዛ ልትመነዘር እና ኦርቴልህን (የኦሪዮን የፍርድ ደብዳቤህን) ተሸክመህ ወደ ብይንህ ልታመራ ትችላለህ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የነበረው የእውቀት እና የልምድ አቅም በዙሪያው ካሉት የተሻለ መሆኑ ስጋት ሊፈጥር ይችላል የሚል ግምትም አለ፤ ድርጅቱ የተሰራ ሰው አይፈልግም፤ ራሱ የሰራውን የበለጠ ያምናል።
መለስ አለም (ዶር) “ሙሌ መሪ ነው፤” አለ፤ በርግጥም ሙለር መሪ ነው፤ ዘይቤውም የአመራር ምሁራን (tough love) ታፍ ላቭ የሚሉት ፍቅርን እና ኮስታራነትን አጣጥሞ የያዘ አመራር አይነት ነው፤ ሁሉንም ነገር በፍቅር ያደርገዋል፤ የሙለር አመራር ቅኝት ፍቅር ነው፤ ይሁን እና ግን መስመር ማለፍ አይቻልም፤ ሲቆጣም በዛው ልክ ነው፤ ቁጣውም ከሥራ እና ከሥራ ጋር ብቻ ነው፤ ለማኔጀመንት ስብሰባ ተቀምጠን አንድ ሰው ዘግይቷል፤ ሲቪል ነው፤ (ታጋይ አልነበረም)፤ ስብሰባውን መጀመር አልቻልንም፤ “ጥሪው ባክሽ፤” አለ፤ አጀንዳውን ይዞ ገባ፤ “ምንድን ነው?” አለና ተግሳጽ ጀመረ፤ ሰውየው ደነገጠ፤ ሙለር ግን መልሶ ሳሳለት እና ሊጠነክርበት አልወደደም፤ የሙሉጌታ ቁጣ አይመሽም። የስብሰባን ወሳኝነት ተናገረ እና እንዳይደገም አለ፤ በዛች የመክፈቻ ተግሳጻዊ ንግግር ሙለር ትምህርት ትቶ አለፈ፤ ከሙለር ጋር መሰብሰብ ትምህርት ቤት መቀመጥ ነበር፤ ሙለር ስብሰባን ተወዳጅ እና ተናፋቂ ያደርገዋል።
ህወሓት ውስጥ እንደሙለር አይነት ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ በተለይም የድርጅቱን ገጽታ ከፍ በማድረግ ደረጃ በተለምዶ አኗኗራቸው እና ስብዕናቸው የግንኙነት መስመር መዘርጋት የሚችሉት በጣም ጥቂት ናቸው፤ በድል ማግስት ሃሴት በ1980ዎቹ የህወሓት እግር መትከል ሂደት ውስጥ በትልቅ ተስፋ የተሞሉ እና “ነገ መልካም ይሆናል፤” የሚል እምነት የሚያጋቡ እና ሲተጉ የነበሩ እንደ እቁባይ በርሀ፣ ሙሉጌታ ገሠሠ እና (ዕጣ ፈንታ በሌላ ረድፍ እስኪያስቀምጠው ድረስ ተስፋዬ ገብረኣብ) ወዘተ አይነት ትንታጎች የማይፋቅ አሻራ በሚዲያው፣ በኪነጥበቡ እና በስነጽሁፍ አለም አምባ ላይ የነገሱት ፈርጦች የተከሰቱበት ዘመን ነበር።
ስንቶቻችን እንዳስተዋልነው ባላውቅም እነዚህ ወጣት ዘርፈ-ብዙ ሞያ መሪዎች ትልልቅ የሃገር ባለውለታዎች እየሆኑ ነበር፤ ለነገሩ እንኳንስ እኛ በደም እና በአጥንታቸው ያገለገሉት ድርጅት (ህወሓት) እንኳን በቅጡ የተረዳቸው አይመስለኝም፤ አለመታደል ሆኖ የጎደለው ላይ እንጂ ያለው ላይ አተኩረን አናመሰግንም፤ መለስ አለም በመታሰቢያው ዝግጅት ላይ “ሙሉጌታን እወድሃለሁ፤” አልኩት፤” አለ፤ ለሰዎች ያለንን አክብሮት የመግለጽ ጥንውታችን መቼ እንደሚራገፍ ባላውቅም ጅማሮው ግን መልካም ነው።
ስለሙሉጌታ ካነሳሁ አይቀር ስለእቁባይ በርሀ አንድ ነገር ብዬ ልለፍ፤ እቁባይ ከጅምሩ “ደብረያሬድ የኪነጥበብ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ” የሚል ተቋም በማቋቋም ኪነጥበቡን መክሊቱ አድርጎ መንገድ ቀይሶ በኋላም ወደ ሜጋ ኪነጥበባት አሳዳድጎ በሁሉም የኪነጥበብ ዘርፎች፣ በሙዚቃ፣ በቲያትር፣ በፊልም፣ በመጽሓፍት ህትመት እና በስዕል ሥራዎች ዘርፎች በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል፤ በርካታ ወጣቶችን በማሰልጠንም ብቃታቸው እንዲወጡ ማድረግ ችሏል፤ እመቤት ወልደገብርኤል፣ ፀደኒያ የደብረያሬድ ውጤቶች ናቸው፤ በኮፒራይት መብት ጥበቃ ዙሪያም እቁባይ ማንም የማይስተካከለው ተግባራትን አከናውኗል፤ (በርግጥ የመጀመሪያው የደብረያሬድ ኪነጥበብ ሥራዎች መጽሔት የ“ፈርጥ” ሽፋን ርዕስ የኮፒ ራይት ጉዳይ ነበር፤ ደርግ ኪነጥበብን ለስርዓቱ ተጠቅሞበት ከሆነ እቁባይ ስርዓቱን ለኪነጥበብ እድገት የተጠቀመ እናም የተሳካለት ሰው ነበር፤ ወደ ፋና ልመለስ።
Ohad Benami - ኦሃድ ቤንዓሚ
ይቀጥላል

1 year ago