Logo
YenetaTube
ፍልሰታ የኦርቶዶክሳውያን የደስታ በዓል ነው።

የፆሙ ወቅት በክረምት ወራት ብሎም ትምህርት በሚዘጋበት ወቅት እንደመሆኑ በበርካታ ታዳጊዎችና ወጣቶች ዘንድ ተወዳጅና ከሌሎች አፅዋማት በተለየ ልዩ ትዝታ የያዘ ነው።

ፆመ ፍልሰታ የእናታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን እረፍት፣ የቅዱስ ሥጋዋን ማረፍ፣ ደግሞም ትንሳዔዋና እርገቷን እያሰብን የምንፆመውና በስተመጨረሻም ሐዋርያት ያዩትን ክብር እያሰብን የምናከብረው በዓል ነው።

በቅድስት ድንግል ማርያም ሞትና ትንሳኤ እንዲሁም እርገት ውስጥ እግዚአብሔር ምን ያህል አብዝቶ እንደወደደንና እርሱ የኛን ሥጋ ነስቶ ሞታችንን በመሞት በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ማረጋገጡን የምናረጋግጥበትም ነው። ለዚህም ነው ቤተክርስቲያን ትንሳኤዋን እንደ ልጇ ትንሳኤ እናከብር ዘንድ የምታስታውሰን።

ስለ ትንሣኤ ሲነሳ ከዋናው ትንሳኤ ሙታን እስቀድሞ በሰው ልጅ የቀንተቀን እንቅስቃሴ ውስጥ ብዙ ትንሳኤዎች ያስተናገዳሉ። ሞት ከተሰኘች ሃጢአት በንስሃ ይነሳል። እንዲሁም ከድካምና ከስንፍና የመንፈስ ትንሳኤን ገንዘብ በማድረግ ወደ ብርታቱ ይመለሳል።

በዘመናችንም ለኦርቶዶክሳውያን በተለይም ለወጣቱ ትውልድ ትንሳኤ ከሚሰሩ ተቋማት አንዱ የመክሊት ግብረሰናይ ማኅበር ነው። ማኅበሩ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማሳደግ የወጣቱን፣ የቤተክርስቲያንንና የኢትዮጵያን ትንሳኤ የማየት ርዕይ ይዞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር ዋና ክፍል በመዝገብ ቁጥር 004/16 የካቲት 1 2016ዓ.ም የተመዘገበ ማህበር ነው።
የማኅበሩ የክብር አምባሳደር ሊቀ መዘምራን ይልማ በቅርቡ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል Yilma Hailu የለቀቀውን ደሀ ራሱን ላንተ ይተዋል የሚል መጠሪያ ያለውን አዲስ አልበም ሙሉ ገቢ ለማኅበሩ የሰጠ ሲሆን በወጣቶችና ህፃናት ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ፆመ ፍልሰታ ዝማሬዎቹን በማዳመጥ እና ከታች ባሉ ማስፈንጠሪያዎች ማኅበሩን በመደገፍ አዲሱ ዓመት በወጣቶች ህይወት ላይ ትንሳኤ የሚታይበት እንዲሆን ያድርጉ።

በብር ለመለገስ፡ https://chapa.link/donatio...
በዶላር ለመለገስ፡ https://chapa.link/donatio...

CBE: 1000625419348
Ahadu Bank: 0005202010101
ለበለጠ መረጃ፡ https://meklitha.org/join

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.