ማን ያሸንፋል?
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመት የመጀመሪያ ሳምንት በዕለተ እሁድ ማንቸስተር ዩናይትድ በግዙፉ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም አርሰናልን ያስተናግዳል።
ሁለቱ የእግር ኳስ ፈርጦች በእንግሊዝ እግር ኳስ ስማቸው የገነነ ጉምቱዎች በአንድ ከተማ ሳይገኙ ለባላንጣነት የተጎራበቱ የስኬት ተቀናቃኞች ናቸዉ ፡፡
የቀድሞ ኃያልነታቸውን ለሊቨርፑልና ለማንችስተር ሲቲ አስረክበው የበይ ተመልካች ለመሆን የበቁት የሰሜን ለንደን ፈርጦቹ አርሰናሎችና የላንክሻየሩ ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ መክፈቻ ይገናኛሉ፡፡
ዛሬ ምሽት አይኖች ሁሉ አስደናቂ ፍልሚያ በተደገሰበት ግዙፉ ኦልድትራፎርድ ይሆናሉ፡፡ የብዙኃኑን ልብ ሰቅዞ የሚይዘው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አንደቀደመው ዘመን አጓጊነቱ ባይጎላም አሁንም ግን በብዙዎች ዘንድ ግን ተጠባቂ ነው፡፡
በአገራችን አግር ኳስ አፍቃሪያንን ለሁለት ከፍሎ በሰልፍ የሚታይ የተመልካቹ ሁሉ ጉጉት የሆነ ስፖርታዊ ቲያትር ነው፤ የሁለቱ ቡድኖች ፍልሚያ ሳቅና ደስታ፤ የሜዳ ላይ ጸብና ፍልሚያ ሚያጅበው ማራኪ ቴያትር ነው፡፡
በስኮትላንደዊው የውጤት ባለሟል ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ከፕሮፌሰሩ አርሰን ዌንገር አርሰናል ጋር የነበራቸው ከፍተኛ ትንቅንቅ እንዲሁም የሁለቱ ቡድኖች ነውጠኛና ተናዳፊ አምበሎች ሮይ ኪንና ፓትሪክ ቬራ የመሪነት ፍልሚያም አይዘነጋም፡፡
በ2011/12 የውድድር ዘመን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የአርሰን ቬንገሩ አርሰናል 8 ለ 2 የተሸነፈበት ታሪካዊ ጨዋታ ነሐሴ ወር በደረሰ ግዜና ሁለቱ ቡድኖች ሲገናኙ የደጋፊዎች መበሻሸቂያ ነው፡፡
ቡድኖቹ ከሁለቱ ታላላቅ አሠልጣኞች ሰር አሌክስ ፈርጉሰንና አርሰን ቬንገር መልቀቅ በኃላ ታላቅነታቸው ከድቷቸው፤በውጤት እጦት ሲቸገሩ ታይቷል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በተለምዶ ቶፕ 6 ተብለው ከሚጠሩት ቡድኖች ጋር በሚያደርገው ጨዋታ አርሰናል ሽንፈትን አላስተናገደም፡፡
ከአውሮፓ ውድድር ውጪ የሆኑትና የሀገር ውስጥ ውድድር ብቻ ተሳታፊ የሆኑት ማንችስተር ዩናይትዶች ያለፈውን አስከፊ የውድድር ዘመን መጥፎ ትዝታ በተሻለ ለመቀየርና የደጋፊው ልብ ላይ የነበረውን የውጤት ማጣት ቁስል የማጥፋት ተስፋን ሰንቀው የሊጉ ዋንጫን ለማሸነፍ የሚገመተውን የሰሜን ለንደኑን ፈርጥ አርሰናል ለማሸነፍ አሞሪምና ሰራዊታቸው ተዘጋጅተዋል ፡፡
ሁለቱም ቡድኖች በእንግሊዝ የእግር ኳስ ታሪክ በሊግ መጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ሲገናኙ የዘንድሮው ለሁለተኛ ግዜ ሲሆን ለመጀመሪያ ግዜ ከዚህ ቀደም በ1989-90 የውድድር ዘመን በኦልድትራፎርድ ባደረጉት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ 4 ለ 1 አሸንፏል፡፡
አርሰናሎች ለ11 ተከታታይ ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ 14 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል ነገር ግን ያሸነፉት ሁለቱን ብቻ ነው፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ 22 ግዜ በማሸነፍ ባለሪከርድ ነው፡፡
በአርሰናል በኩል የቡድን ዜናዎችን ስንመለከት ጋብሬል ጄሱስ በጅማት ጉዳት እስከ መስከረም ድረስ ወደ ሜዳ የማይመለስ ሲሆን የሊያንድሮ ትሮሳርድ መሰለፍ አጠራጣሪ ሆኗል። ሆኖም ሚኬል አርቴታ ከሁለቱ ተጨዋቾች ውጪ ሙሉ ስብስቡ ለጨዋታው ዝግጁ ነው ሲል ተናግሯል።
አሰልጣኙ አክሎምል አርቴታ ስለ ትሮሳርድ ''እንደማስበው ትሮሳርድ ተሻሽሏል፤ ነገ አብሮን ልምምድ ማድረግ ይችላል ብየ አስባለሁ፣ ዝግጁ ይሆናል'' ሲል ተናግሯል።
በማንችስተር ዩናይትድ በኩል አዲሶቹ ፈራሚዎች ቤንጃሚን ሴስኮ፣ ማቲያስ ኩንያ እና ብሪያን ምቤሞ ለመጀመሪያ ግዜ በቋሚነት መሰለፍ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኑሰይር ማዝራዊ እና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ግን በጉዳት ምክኒያት በጨዋታው ላይ አይሠለፉም።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ተገኝተው ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ''ማዝራዊ እና ማርቲኔዝ አይጫወቱም፣ነገር ግን ዜርክዚ ኦናና እያገገሙ ነው፣ ለዚህ ጨዋታ የመሰለፍ ዕድል ይኖራቸዋል፤ '' ሲል ተናግሯል።
✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ

12 months ago