Logo
Getu Temesgen
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ታሪክ በኢንሳይክሎፔዲያ መልክ ሊዘጋጅ ነው
#ethiopia | የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር የጀግኖች አርበኞችን ታሪክ በሳይንሳዊ መንገድ ለማጥናትና በኢንሳይክሎፔዲያ መልክ ለማዘጋጀት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ የተዋደቁ አርበኞች ታሪክ በትክክለኛና በተሟላ መንገድ ተደራጅቶ እንዲሰነድና ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ያለመ ነው።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ስምምነቱ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖችን ታሪክ በጥናትና ምርምር በሳይንሳዊ ዘዴ በመምራት ፣ በማዘጋጀት እና በማሳተም ለትውልድ ማስተላለፍ ጠንካራ አገራዊ አንድነት ለመፍጠርና ቀጣዩ ትውልድ ለአገሩ በአርበኝነት እንዲቆም በእጅጉ ያግዛል ሲሉ የጥናቱን ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡

በፊርማው ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ጥናቱ ጥራቱን ጠብቆ አንዲካሄድ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው ተገቢውን ባለሙያ፣ ሃብትና አመራር እንደሚመድብ አስረድተዋል፡፡(AAU)

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.