Logo
SeledaPost
አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልን ጎበኘች

ታዋቂዋ አሜሪካዊት ተዋናይትና ሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ አንጀሊና ጆሊ በኢትዮጵያ የሚገኘውን
የቅዱስ ጴጥሮስ ልዩ ሆስፒታልን ጎብኝታለች።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ሆስፒታሉ በመድኃኒት የሚቋቋም ቲቢ (MDR-TB) ሕክምና ዙሪያ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች መመልከትና ለውጦችን መገምገም ነበር።

የጉብኝቱ ዋና ትኩረት:-

በጉብኝቷ ወቅት አንጀሊና ጆሊ የሆስፒታሉን የቲቢ እና የመድኃኒት የሚቋቋም ቲቢ (MDR-TB) ሕክምና መስጫ ክፍል፣ ላቦራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ጎብኝታለች።

የቀድሞ ጉብኝቷን በማስታወስ፣ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን በማድረጉ በጣም መደሰቷን ገልጻለች።

በተጨማሪም ሆስፒታሉ ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ገልጻ፣ በቀጣይ በGlobal Health Committee (GHC) በኩል ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች።

የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ፣ አንጀሊና ለቲቢ ሕክምና ላሳየችው ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነትና ለጋስነት ምስጋና አቅርበዋል።

አንጀሊና ጆሊ ከትወና ሥራዋ ባሻገር ለዓለም አቀፍ ስደተኞችና ሰብአዊ መብቶች ጥብቅና በመቆም ለ20 ዓመታት ያህል በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) የበጎ ፈቃድ አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ሰፊ ሰብአዊ ሥራዎችን በማከናወን ትታወቃለች።
Seledadotio
Seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.