Logo
YenetaTube
ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ኢትዮጵያ መጣች !

‎ተወዳጇ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ የሆነችዉ የሆሊውድ ፈርጧ አንጀሊና ጆሊ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን መጎብኘቷ ተነገረ።

‎ተዋናይቷ ባደረገችው ጉብኝት በዋነኝነት ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

‎በጉብኝቱ ላይ አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢና መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና አገልግሎት መስጫ ዋርድ ፣ ላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን መመልከቷም ተገልጿል ።

‎አንጀሊና ወደ ሆስፒታሉ ከረጅም ጊዜያት በፊት መጥተታ እንደነበር በማስታወስ በአሁኑ ጉብኝቷ ላይ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች አምጥቶ መመልከቷ እጅግ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች ።

‎አክላም ሆስፒታሉ ድጋፍ ቢደረግለት በቀጣይ የተሻለ ‎አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት በሚያስችለው አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዳለ በጉብኝቱ ላይ መገንዘቧን ገልፃለች ገልፀዋል።

‎በተጨማሪም በሆስፒታሉ በቲቢ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገኘው እድገት በእጅጉ የሚደነቅ እና የሚያስተማምን ስለሆነ በቀጣይ በጂ.ኤች.ሲ (Global Health Committee (GHC)) በኩል ድጋፍ እናደርጋለን ብላለች።

‎ሲል ተቋሙ /ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል / በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል ።


10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.