Logo
FastMereja
የተሰረቀ የመኪና ስፖኪዮ የሚረከበው ተያዘ

የተሰረቀ የመኪና ስፖኪዮ ከሌባ በመቀበል ሲያከማች የነበረን ተጠርጣሪ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የለሚኩራ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በመኖሪያ ቤቶች እና መዝናኛ ስፍራዎች ላይ በመንቀሳቀስ የግል ተበዳዮች ተሽከርካሪዎቻቸውን አቁመው በሚሄዱበት አጋጣሚ የሰዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል የመኪና ስፖኪዎችን እየተገነጠሉ የስርቆት ወንጀል ሲፈፀም ነበር።

የሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የግል ተበዳዮች በተደጋጋሚ አቤቱታ በመቀበል፣ የምርመራ ቡድን በማደራጀት፣ በሰራው ኦፕሬሽ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አሜሪካን ግቢ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በሸራ ቤት ውስጥ የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን ከወንጀል ፈፃሚዎች እንደሚቀበል በተገኘ መረጃ የፍርድ ቤት መበርበሪያና መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ብርበራና ፍተሻም ተደርጓል፡፡

በተደረገው ብርበራና ፍተሻም 59 የል ልዩ ተሸከርካሪዎችን ስፖኪዮ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር ሊያዝ መቻሉንም ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ተገቢውን ምርመራ የማስፋት ተግባሩን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመኪና ስፖኪዮ ተሰርቆብኛል የሚል ማንኛውም ግለሰብ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ዕቃውን መምረጥና መረከብ የሚችል መሆኑም ተገልጿል፡፡

የተሽከርካሪ ባለቤቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ስርቆት ሲፈፀምባቸው በደላላም ሆነ በግላቸው ከሌባ ተቀባዮች ጋር በመደራደር ንብረታቸውን በገንዘብ የሚገዙ፣ ወንጀለኛውን ለፖሊስ የማይጠቁሙ መሆኑናቸው የመኪና ዕቃ ስርቆት ፈፃሚዎችን የሚያበረታታ ድርጊት መሆኑንም መታዘብ ተችሏል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ወንጀለኞችን በማጋለጥ የወንጀል ድርጊቱ ሲፈፀምበትም በአቅራቢያው ወደሚገኝ የህግ አካል በማሳወቅ ለህግ የበላይነት መረጋገጥ መትጋት እንደሚኖርበትም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.