Logo
YenetaTube
ቀይ ባህርን ከዚህ በኋላ እኔ እጠብቀዋለሁ !/ ግሪክ/

ግሪክ ማጂክ ባህር እና ኢተርንቲቲ ሲ የተባሉ የጭነት መርከቦች በሀዉቲ ጥቃት በቀይባህር መስጠማቸዉን ተከትሎ የቀጠናውን ደህንነት ለማስከበርና መርከቦችን ለመጠበቅ የማዳኛ መርከብ በቀይ ባህር ላይ እንደምታሰማራ ገለፀች ።

በዚህ ወር የየመን የሁቲ ታጣቂዎች በሁለት የግሪክ መርከቦች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን ተከትሎ ግሪክ በባህር ላይ አደጋዎችን ለመርዳት እና የባህር ላይ ተሳፋሪዎችን እና አለምአቀፍ መርከቦችን ለመጠበቅ የማዳኛ መርከብ በቀይ ባህር ላይ እንደምታሰማራ የመርከብ ሚኒስትሯ ገልፀዋል ።

እንደ ዘገባዉ ከሆነ ሁቲዎች ከፍልስጤማውያን ጋር ያላቸውን አጋርነት የሚያሳይ ነው ሲሉ በሚገልፁትና ከእስራኤል ጋር ግኑኝነት አላቸዉ በሚል በዚህ ወር ብቻ ሁለት የላይቤሪያ ባንዲራ ያደረጉ፣ በግሪክ የሚመሩ ማጂክ ባህር እና ኢተርንቲቲ ሲ የተባሉ የጭነት መርከቦች በየመን ማስጠሙን ተከትሎ ግሪክ ይህን ዉሳኔ ለመወሰን እንተገደደች ተገልጿል ።

የመርከብ ጉዳይ ሚኒስትር ቫሲሊስ ኪኪሊያስ “ግዙፉ” ተብሎ የሚጠራው እና በሄለኒክ የቱግቦት ባለቤቶች ማህበር የቀረበው የማዳኛ መርከብ “የግሪክ ንብረት የሆኑ መርከቦችን እና የግሪክ መርከበኞችን ይደግፋሉ ፣ ይጠብቃሉ እና ይረዱታል” ብለዋል ።

ግሪክ በቀይ ባህር ለማሰማራት ያሰበችው ጂያንት መርከብ በ14 የግሪክ መርከበኞች ልዩ ባለሙያተኛ የሚተዳደር ሲሆን 16,000 የፈረስ ጉልበት ያላቸው አራት ሞተሮች ያሉት በፍለጋ እና በማዳን ስራዎች የባህር ብክለትን ለመከላከል ፣እንዲሁም የእሳት አደጋ መቋቋም የሚችልና እጅግ አስከፊ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ በመርከብ መጓዝ እንደሚችል የመርከብ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.