Logo
SeledaPost
በኤርትራ ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ

የኤርትራ መንግሥት በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ርህራሄ የለሽ ጥቃት አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያስቆም የቀይባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ጠይቋል።የኢሳይያስ መንግሥት:-

🔹በአፋር ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ እንዲፈፀም ስፖንሰር አድርጓል።

🔹በግዳጅ መሰወር፣ የጅምላ እስራት እና ለረጅም ጊዜ በማይታወቅ ቦታ እስራት መፈፀም።

🔹ለሀገር አቀፍ አገልግሎት በሚል በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ካምፕ መውሰድ።

🔹ሆን ተብሎ በቀይ ባህር አካባቢ የሚገኙ የአፋር ክልል እስትራቴጂካዊ ግዛቶችን ህዝብ እንዳይኖርባቸው ለማራቆት በርካታ ሰዎችን አፈናቅሏል።

🔹ማሰቃየት፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች ፈፅሟል ብሏል።

ፓርቲው የኤርትራ መንግሥት በአፋር ህዝብ ላይ እየፈፀመ ላለው ወንጀል አለምአቀፉ ማህበረሰብ ነገ ሳይሆን ዛሬ፣ቀጣይ አመት ሳይሆን በዚህ አመት በአስቸኳይ በኤርትራ መንግሥት ላይ ወታደራዊ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እንዲወስዱ በአስቸኳይ ጥሪ አቅርቧል።
Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.