ባልተረጋገጠ መረጃ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው የአንዲት ግለሰብ አቤቱታ ሐሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በድጋሚ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ ቀደም ' በእኔና በልጆቼ ላይ ጥቃት እየተፈፀመብን ነው '' በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ ያስተላለፈችን ግለሰብ ጉዳይ ተገቢው ትኩረት ሰጥቶ የግለሰቧን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ምርመራ ማድረጉን የሚገልፅ ዜና በገጻችን መልቀቃችን ይታወቃል፡፡
ወ/ሮ ሰርካለም አስራት ነሃሴ 19 ቀን 2016 ዓ/ም በልጇ ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት እንደተፈፀመበት እና እሷ ላይ ጥቃት ሊፈፀምባት መሆኑን ለለሚኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማመልከቷን ተከትሎ ፖሊስ በወንጀሉ የተጠረጠውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ጥቃት ደርሶበታል የተባለውን ህፃን ወደ አበበች ጎበና መታሰቢያ ሆስፒታል መላኩን እንዲሁም ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልኮ በህፃኑ ላይ ምንም አይነት የግብረ ሰዶም ጥቃት እንዳልተፈፀመበት በሀኪም ማስረጃ እንደተረጋገጠም የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር መስፍን በላቸውን ዋቢ አድርገን መረጃውን ለህዝብ ግልፅ ማድረጋችን የሚታወስ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ/ም ግለሰቧ ተመሳሳይ አቤቱታ ማቅረቧን ተከትሎ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ማድረጉንና ታዳጊው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ ተደርጎለት ጥቃቱ እንዳልተፈፀመበት ተረጋግጧል፡፡
በአበበች ጎበና ሆስፒታል የተቀናጀ የሴቶችና ህፃናት ህክምና ክፍል የህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ወገኔ አሰፋ ለህፃኑ ሁለት ጊዜ ምርመራ እንደተደረገለትና ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትም አስረድተዋል፡፡
ግለሰቧ እና የ12 ዓመት ልጇ በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ሲከታተሉ እንደነበርና ህክምናውን ሳይጨርሱ ማቋረጣቸውን ፖሊስ በማስረጃ ያረጋገጠ ሲሆን ወንጀሉን ፈጽሟል ተብሎ በግለሰቧ አቤቱታ የቀረበበት አቶ ተወልደ ከበደንም ጉዳዩን ለማጣራት አምስት ቀን አስሮት እንደነበረ እና የህክምና ውጤቱን ተከትሎ በዋስ መለቀቁም ይታወሳል።
ነገር ግን ግለሰቧ አሁንም ድረስ ፍትህ እንዳላገኘች በመግለፅ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመውጣት ሀሰተኛ መረጃን እያሰራጨች ትገኛለች። ከዚሁ ጎን ለጎን አንዳንድ መረጃውን ከአንድ ወገን ብቻ በመስማት የሚያስተጋቡ ህገ-ወጥ ግለሰቦችም መኖራቸውን የሚገልጸው ፖሊስ በህግ አግባብ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። ባልተረጋገጠ መረጃ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው የግለሰቧ አቤቱታ ሐሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በድጋሚ እያስታወቀ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት በህግ የሚያስጠይቅ በተለይም በሰዎች ማህበራዊ ህይወት ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና የሚያሳድርና የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
አዲስ አበባ ፖሊስ

1 year ago