Logo
Getu Temesgen
የታዝማ የልብ ህክምና ቡድን ለአምስት አመት ታዳጊ የተወሳሰበ የልብ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ አከናወነ!

በተደጋጋሚ ስኬታማ እና ውስብስብ ቀዶ ህክምናዎችን በማድረግ የሚታወቀው ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ህክምና ልዩ ማዕከል፣ አሁንም በድጋሚ ለአምስት ዓመቱ ታዳጊ እጅግ ከባድ እና ህይወት አድን የሆነ የልብ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

ይህ ታዳጊ ከተወለደ ጀምሮ Type IV Truncus Arteriosus በተባለ ከባድ የልብ ህመም ሲሰቃይ ቆይቷል። ይህም ከተወለደ ጀምሮ የተከሰት ውስብስብ የልብ ችግር ሲሆን፣ የታችኛው የቀኝ እና የግራ የልብ ክፍል የሚለየው የልብ ግድግዳ ላይ ክፍተት (ventricular septal defect)፣ ወደ ሳንባ የሚሄዱት የልብ ቧንቧዎች የሚነሱበት ቦታ የተዛባ መሆን፣ እና ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ ሳንባ ደም የሚወስደው ትልቁ የደም ቧንቧ (pulmonary artery) አለመፈጠር (pulmonary atresia) ናቸው።

ታዳጊው ባለፉት ዓመታት በሳንባ ምች ምክንያት በተደጋጋሚ ሆስፒታል ገብቶ የነበረ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የከንፈር መሰንጠቅ (cleft lip) ለተባለ የተፈጥሮ ችግር ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል።

ሆኖም ግን በጊዜው በማዕከላችን የተገኘው በኢንፌክሽን ምክንያት ቢሆንም ከኢንፌክሽኑ ህክምና በኋላ ቀዶ ህክምና ማከናወን ግድ ስለነበር፣ እጅግ ልምድ ባላቸው የአዋቂና የህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪም ዶ/ር ሲሳይ በቀለ የተመራው የማዕከላችን የልብ ህክምና ቡድን በልጁ ልብ ውስጥ የነበሩትን የአፈጣጠር ችግሮችን ለማስተካከል እጅግ በጣም የተወሳሰበ የሆነውን Truncus repair with RV-PA conduit + confluence plasty የተባለ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል።

ቀዶ ህክምናውም በታችኛው የልብ ግድግዳ መካከል ያለውን ትልቅ ክፍተት መዝጋት፣ የሳንባ ደም ስሮች የተዛመዱበትን ስፍራ ማስተካከል፣ እና ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ ሳንባ በትክክል እንዲፈስ በእጅ የተሰራ ቧንቧ (RV-PA conduit) በመጠቀም አዲስ መንገድ መፍጠርን ያካትታል።

እንደተለመደው፣ ይህ የቀዶ ህክምና በተቀላጠፈ እና በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ላደረጉ የታዝማ የልብ ቀዶ ህክምና ቡድን ምስጋናችንን እያቀረብን፣ ቀዶ ህክምናው የተደረገለት ታካሚያችን በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ላይ ሆኖ ወደ ቤቱ መመለሱን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

ታዝማ የጤናማ ልብ አርማ!

ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ህክምና ልዩ ማዕከል

Book an appointment!

Contact us
9893 /+251954886225
Follow us:
Facebook: https://www.facebook.com/t...
Instagram: https://instagram.com/tazm...
Tiktok: https://www.tiktok.com/@ta...
Telegram: https://t.me/TazmaCenter

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.