ዳሽን በእንጦጦ
#ethiopia Iዳሸን ባንክ በእንጦጦ ተራራ የአገር በቀል ችግኞች ተከላ መርሃ-ግብር አከናወነ።
የዳሸን ባንክ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ የተለያዩ የሀገር በቀል የዛፍ ችግኞች ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ።
የችግኝ ተከላው የባንኩ የአካባቢ፣ ማህበራዊ እና አስተዳደር (Environmental, Social, and Governance- ESG) የአየር ንብረት ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ ይህም ባንኩ ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጠናክር ነው።
ዳሸን ባንክ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ጋር በመተባበር ላለፉት አመታት በእንጦጦ ተራራ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አገር በቀል ችግኖችን በመትከል ለብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ የተራቆቱ ስነ-ምህዳሮች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ እንዲሁም ለአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡
የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃግብር ባንኩ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ትግል የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት ተግባራትን በማስቀጠል የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎችን ለመከላከል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ በንግግራቸው “እንደ ዳሸን ባንክ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያለን ቁርጠኝነት ባንኩ ምን ያህል ለአካባቢ ጥበቃ እና ለህብረተሰቡ ዘላቂ እሴት ለመፍጠር እንደሚተጋ ያሳያል” ብለዋል።
“እንደዚህ ባሉ መርሃግብሮች መሳተፋችን እንደ እኛ ያሉ ባንኮች የአየር ንብረት ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ለትውልድ ቀጣይነት ያለው ልማት በማጎልበት ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንደሚችሉ እናሳያለን።” ያሉት አቶ አስፋው፣ አክለውም የወደፊቷ ኢትዮጵያ አረንጓዴና ዘላቂ ብሩህነትን በመገንባት ረገድ በተጨባጭ በአርአያነት እየመራን ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ቦርድ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ከማህበሩ ጋር በመተባበር ባለፉት አመታት ያከናወናቸው ተግባራት እና ያበረከተው ድጋፍ ለሌሎች ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።
ዳሸን ባንክ የአካባቢ፣ ማህበራዊ እና አስተዳደር (ESG) መርሆችን ከአገልግሎቱ ጋር በማዋሃድ፣በተለያዩ የሰብአዊ፣ የጤና እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በማህበረሰብ ልማትና ማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ተግባራት ላይ ግንባር ቀደም ሆኖ እየሰራ ይገኛል።
በተጨማሪም ዳሸን ለዘላቂ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት በሚያንፀባርቁ የአካባቢ፣ ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ ተግባራት ላይ በጥልቀት በመሳተፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እንደዚህ አይነት ተግባራቱ ለአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ ከማድረግ ባለፈ የስራ እድል በመፍጠር እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት ማህበራዊ አጋርነትን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

1 year ago