መኮንን ሃብተ ማርያም(መ/አ)
ሕይወትን በአንድ እጅ ~ [ ግለ ታሪክ ]
#ethiopia | በአየለ እሸቱ የተጻፈው በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተጋድሎ ውስጥ የመ/አ መኮንን ሃብተማርያም ግለ ታሪክ ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ብራስ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ የባህል ማዕከል ከቀኑ 7:00 ሰዓት ይመረቃል።
***
ስለባለታሪኩ
መኮንን ምንም አይነት ፈተና ሳይሰብረውና ከዓላማው ሳያሰናከለው በአየር ኃይል በኋላም በሲቪል አቪየሽንና በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በውጪም በትራንስፖርት ካናዳ ዐቢይ ግልጋሎትን ፈፅሟል። ለብዙ ሰው በሁለት እጅ እንኳ አስቸጋሪ የሆነውን ህይወት መኮንን ውጣ ውረዱን ቁብ ሳይለው በአንድ እጁ ብቻ ዘለቀበት፡፡ ባለቤቱ አጠገቡ ባልነበረችበት ወቅት ለአምስት ልጆቹ ምግብ አብስሎና ተንከባከቦ ትምህርት ቤት አመላልሶ ያለምንም ረዳት አሳደጋቸው።
ይህ የመ/አ መኮንን መጽሐፍ የእውነትን፣ የፅናትን፣ የአርበኝነትና ለመከራ ያልተንበረከከ ህይወትን አሸናፊነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው :: መኮንን በአንድ እጁ ብቻ የመራውን ህይወት በአግራሞት ዕለት በዕለት ስመለከተው ኖሬያለሁ። የፅናትና የስኬት ተምሳሌት በመሆኑ ለትውልድ አርዓያ ይሆን ዘንድ ታሪኩን በመጽሐፍ መልኩ እንዲያቀርብም ጎትጉቼዋለሁ። መኮንን ሁልጊዜም አድማጭነው:: ስለዚህም ይህንን ስጦታ ለትውልድ በማበርከቱ እጅግ ሊመሰገን ይገባል፡፡
ተስፋዬ አብዲ (አምባሳደር)
በአየር ኃይል፣ በመከላከያ ሚኒስቴርና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገለገሉ ዲፕሎማት
***
በህይወቴ ብዙ የማደንቃቸው ሰዎች አሉ፡፡ ግን መኮንን በዚህ ሁኔታ ኑሮውን አስተካክሎ ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ ሳስብ ያስገርመኛልም፣ አደንቀዋለሁም። ማንም ሰው ይህንን ያደርጋል ብዬ በሃሳቤ ኖሮ አያውቅም። ያሳለፈውን ፈታኝ ጊዜ ሳየው ሊደረግ የማይቻል መስሎ ነበር የሚታየኝ። ያኔ አደጋ በደረሰበት ጊዜ ይህ ሰው አበቃለት፣ ህይወቱ ተበላሸ፣ እንግዲህ እንዴት ሊኖር ነው? ብዬ እንዳላዘንኩኝ ዛሬ ከብዙ ትግል በኋላ እዚህ መድረሱ እጅግ ያስደንቀኛል። ማንንም ሰው በዚህ ደረጃ አስቤም፣ አይቼም አላውቅም። መኮንን ትሁት፣ በሁሉም አንፃር የተሟላ ስብዕና ያለው ሰው ነው:: ያደረገው ትግልና የደረሰበት ደረጃ በቃላት ከሚነገረው በላይ ነው :: ታሪኩን በመጽሐፍም ብቻ ሳይሆን ፊልምም ሆኖ የሚታይ አስደናቂ ታሪክ እንደሆነ ይሰማኛል።
ውብሸት ተፈራ (ኮሎኔል)
አየር ኃይልና ሲቪል አቪየሽን ያገለገሉ
***
መኮንን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወጥነት ያለውና ዓለም አቀፋዊነቱን የጠበቀ የክንውን መመሪያና የፖሊሲ ማኑዋል እንዲኖረው ለማድረግና ያንንም ወደ መሬት ለማውረድ ከፍተኛ ተግባር ከማከናወኑም በላይ በሴፍቲ ጉዳይ አየር መንገዱን በቅርበት ዕለት በዕለት በመከታተል በተጨባጭ የታዩ ተግባሮችን አከናወኗል፡፡ አየር መንገዱ እያደገና እየሰፋ ሲሄድ ይበልጥ ጠንካራና ውጤታማ ሊሆን የቻለውም በዚያን ጊዜ የነበሩ፣በሳል ባለሙያዎች ለአየር መንገዱ አድጎት አስተማማኝ መሰረት በመጣላቸው ነው። ያ ቢሮ ጠንካራና ራሱን ችሎ በትኩረት የሚሠራ ከፍል እንዲሆን ማድረግ የተቻለው መኮንን ከመጣ በኋላ ነበር። እኔ ሁልጊዜም አብሬው ብሆንም፣ በሌሎች መደበኛ ተግባሮቼ የተነሳ አብዛኛውን ተግባር ያከናውን የነበረው እሱ ነበር፡፡ አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅና ወደፊት ተመልካች እቅዶችን በመዘርጋት የሴፍቲ ክፍሉ የሚጠበቅበትን ተግባር በአግባቡ እንዲወጣና ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ለማድረግ የነበረው ትጋት ሁልጊዜም ያስደንቀኝ ነበር። መኮንን ሰው መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በጥልቀት እንድገነዘብ ያስቻለኝ፣ ተግባርን በትጋት የማከናወንን አስፈላጊነት የተማርኩበት ሰው ነው::
አስረስ አርኢያ (ካፒቴን)
ለበርካታ ዓመታት አየር መንገድን በካፒቴንነት ያገለገሉ

11 months ago