የአፍሪካ ልማት እንጂ ኒኩሊየር አያሴፈልጋትም ! /ናይጀሪያ /
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ የአፍሪካ አሳሳቢ ጉዳዮች ድህነትን እና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ላይ እንጂ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አቅምን በማጎልበት ላይ እንዳልሆነ እንዲሁም በዚህ ወቅት ለአህጉሪቱ እንደማያስፈልግ መናገራቸው ተሰማ።
ይህንንም ያሉት አጠቃላይ የኑክሌር-ሙከራ-ባን ስምምነት ድርጅት (ሲቲቢቶ) ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ሮበርት ፍሎይድ ጋር ባደረጉት ዉይይት መሆኑ ተነግሯል ።
የአህጉሪቱ ትኩረት በዘላቂ ልማት ላይ መሆኑን በግልፅ የተናገሩት ሼቲማ "ድህነትን እየተዋጋን ነው፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ስነ-ምህዳሮች መካከል ያለውን ግንኙነት በመቃወም ጦርነት እየዋጋን ነው። ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ ጋር በተገናኘ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት የለብንም" ብለዋል
እንደእርሳቸው ገለጻ የኒውክሌር ግጭት ምንም አይነት አወንታዊ ውጤት አያመጣም እና አህጉሪቱ በወታደራዊ አቅም ላይ ከማተኮር ይልቅ የልማት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ሃይሏን እና ትኩረቷን ልማት ላይ እንድታደርግ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ሼቲማም አክለውም አፍሪካ ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ልትውል ትችላለች የሚለው ስጋት መሠረተ ቢስ ነው ሲሉ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማረጋጋት ሞክረዋል። ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒዉስ ድልረገፅ ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

11 months ago