Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#inflationrate📈

የመስከረም ወር 2019 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.9 በመቶ የተመዘገበ ሲሆን ይህም በመስከረም 2018 ዓ.ም ከነበረው 13.2 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አሳውቋል።

የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.8 በመቶ የጨመሩ ሲሆን በዋናነት ፦
👉 አትክልት 11.4 በመቶ፣
👉 ስጋ 22.0 በመቶ፣
👉 የወተት ተዋፅኦዎች እና እንቁላል 17.7 በመቶ፣
👉 ፍራፍሬ 18.5 በመቶ፣
👉 ዘይት እና ቅቤ 18.2 በመቶ፣
👉 ስኳር፣ ማር እና ቸኮሌት 39.8 በመቶ
👉 ዳቦ እና እንጀራ 8.6 በመቶ፣
👉 የምግብ ምርቶች 19.1 በመቶ በመጨመራቸው የተመዘገበ ጭማሪ መሆኑን መረጃው ያሳያል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 15.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ፦
• ትራንስፖርት 16.0 በመቶ፣
• አልኮል መጠጦችና ትምባሆ 18.2 በመቶ፣
• በኮሙዩኒኬሸን 9.6 በመቶ፣
• ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 15.3 በመቶ፣
• ትምህርት 17.8 በመቶ፣
• ጤና 10.9 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 17.6 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia #inflationrate 😎 የነሐሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.1 ሆኖ ተመዝግቧል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት፣ የነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሸበት 15.1 በመቶ መመዝገቡን ይህም በነሐሴ 2017 ዓ.ም ከነበረው 13.6 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱን ገልጿል። የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.9 በመቶ ጨምረዋል። በዋናነት ፦ - አትክልት 12.1 በመቶ ፣…
5 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.