Logo
YeneTube
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

በስልክ ውይይቱ ወቅት አመራሮቹ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እንዲሁም በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል። ይህ ውይይት በእንደገና አዲስ ምዕራፍ ላይ በሚገኘው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ውስጥ በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቅሷል።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ዘላቂ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የሰጠችውን ማረጋገጫ ያደነቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያም በበኩሏ የሁለትዮሽ ትብብሩን ለማጠናከር እና የጋራ ትኩረት በሚሹ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

Fikerassefa Fikerassefa
10 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.