Logo
YeneTube
❗️ሸራሮ ምን እየተካሄደ ነው!!?

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከባድ የአየር ድብደባዎች እየተደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት 2 እና 3 ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ከባድ ድሮን እና የአየር ድብደባዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል።

የኤርትራ ጦር እና የትግራይ ተዋጊዎች ከዋና ዋና ከተሞች ሲወጡ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደህንነታቸው ወደተጠበቁ ቦታዎች እንዳይሸሹ እና ጥቃቶችን እንዳይሰነዝሩ ለመከላከል ቀጣይነት ያለው የአየር ዘመቻዎችን እያደረገ ይገኛል።

ከአዲግራት እስከ ዛላምበሳ፣ ከአድዋ እስከ ራማ፣ እና ሺራሮ አካባቢዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።

ይህንን ተከትሎ በኤርትራ አዋሳኝ ሽራሮ አካባቢ የእሳት አደጋ የተነሳ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወይም ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ ኤርትራ ድንበር እየተዛመተ መሆኑን ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል።

@Yenetube Fikerassefa
13 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.