የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የጋዜጠኞች ስልጠና ተጠናቀቀ ።
ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ለተውጣጡ የስፖርት ጋዜጠኞች የኦሊምፒክ ፅንሠ ሃሳብ፣ መርሆዎችና አስተዋፅኦ፣የኦሎምፒክ ቻርተር፣የስፖርት አስተዳደር እና የስፖርት ጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን ርዕሶች ዙሪያ ለሁለት ቀናት ስልጠናው ተሰጥቷል።
በስልጠናው የተካፈሉ ጋዜጠኞች ሙያዊ አቅምን ለማሳደግ የጋዜጠኞችን እውቀት ለማጎልበት የኦሊምፒክን ቻርተር በተገቢ መንገድ እንዲሁም የስፖርት አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብ ለመረዳት ያግዛል ብለዋል።
የስፖርት ውጤቶችን ከመግለፅ ባለፈ የሚታዩ ችግሮችን በሙያዊ እውቀት በመተንተን፣ የሚዲያ እና የስፖርት አመራሮችን ግንኙነት ማዳበር እና ተጠያቂነትን በማስፈን ተሰጥኦዎችን በማበረታታትና ብሔራዊ ስሜትን በመስበክ ረገድ የስፖርት ጋዜጠኞች ኃላፊነት የላቀ ነው።
የኦሊምፒክ መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳቦችን በመያዝ ጋዜጠኞች በስልጠናው ያገኟቸውን ሀሳቦች በስራዎቻቸው በተሻለ አጎልብተው ይጠቀሙበታል ተብሎ ይጠበቃል ።
ስልጠናውን ኢንስትራክተር ሙሉነህ ግርማ፣ ኢንስትራክተር ዘሪሁን ቢያድግልኝ፣ አምሮት ግዛው (ዶ/ር)፣ ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ዋና ፀሀፊ ገዛኸኝ ወልዴ ሰጥተዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

1 day ago