አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በፎርብስ አፍሪካ 15 አርአያ አፍሪካውያን ተርታ ውስጥ ተካተተ
መጽሔቱ 15ተኛ ዓመቱን በማስመልከት ይፋ ባደረገው ዝርዝር ውስጥ ሃሳባቸው፣ ድምጻቸው እና ሥራቸው በአፍሪካ አኅጉር ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊና ዘላቂ ተፅዕኖ ማሳደር የቻሉ አፍሪካውያንን አካቷል።
ሁለት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች፣ ስምንት የዓለም ሻምፒዮናዎች፣ 27 የዓለም ሪከርዶችን መስበሩ በስፖርት ዘርፉ የተጠቀሱ የተጎናፀፋቸው ድሎች ባለቤት ሃይሌ ገብረስላሴ።
በንግድ መስክ፤ በ "ኃይሌ እና አለም ኢንተርናሽናል" ኩባንያ ስር በሆቴል፣ በመኪና ማምረቻ፣ በሪል እስቴት እና ግብርና ዘርፎች ተሠማርቶ ያገኘው ስኬት በዝርዝሩ ውስጥ እንዲካተት አስችሎታል።
አሊኮ ዳንጎቴ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ እንዲሁም የቀድሞው የኮትዲቯር እና ቼልሲ አጥቂ ዲዲዬር ድሮግባ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ጉልህ አፍሪካውያን ናቸው ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።
@Yenetube Fikerassefa

1 day ago