ወጣቱ ተዋናይ ህይወቱ አልፎ ተገኘ
#ethiopia | በተወዳጁ «ብሬኪንግ ባድ» የቴሌቪዥን ድራማ ሰፊ ዕውቅናን ያተረፈው ወጣቱ ተዋናይ አርጄ ሚቴ በሰላሳ አራት ዓመቱ ሕልፈተ ሕይወት እንዳለፈ ተሰምቷል።
በቴክሳስ ግዛት ሰኞ ዕለት ሕይወቱ ያለፈው ይህ አርጄ ድንገተኛ ህልፈቱ መላው አድናቂዎቹንና የኪነ-ጥበብ ማህበረሰቡን በከባድ ሐዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፣ የድራማው የእርሱ አባት ሆኖ የተጫወተው ብራያን ክራንስተንን ጨምሮ በርካታ የጥበብ ሰዎች ሐዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
አርጄ ሚቴ በልጅነቱ የደረሰበት ሴሬብራል ፓልሲ የተባለ የጤና እክል ቢኖርበትም፣ ይህ ሁኔታ ለስራው እንቅፋት እንዲሆንበት አልፈቀደም።
ከዚህ ይልቅ በቴሌቪዥን ታሪክ ውስጥ እጅግ ተወዳጅ በሆነውና ለረዥም ጊዜ በዘለቀው «ብሬኪንግ ባድ» ድራማ ላይ ዋልተር ዋይት ጁኒየር (ወይም ፍሊን) በመሆን በመጫወት የብዙዎችን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
በድራማው ላይ ከነበረው ተሳትፎ ባሻገር፣ በህይወቱ ያጋጠመውን ፈተና በመጠቀም ለአካል ጉዳተኞች መብትና እኩልነት ጠንካራ ድምፅ በመሆን ሲሟገት የኖረ አርቲስት ነው።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ተዋናዩ ህይወቱ ያለፈው ራሱን አጥፍቶ እንደሆነ ተነግሯል።
የጥበብ ቤተሰቦችና አድናቂዎችም ተዋናዩ ህይወቱን ሙሉ ለአካል ጉዳተኞች መብት መቆሙን እና በኪነ-ጥበብ ስራዎቹ ያስቀመጠውን አሻራ በማስታወስ ሀዘናቸው እየገለጹ ይገኛሉ ይገኛሉ።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

7 hours ago