እነ ጄነራል ታደሰ ወረደ ከእገታ ተለቀቁ ? ወይስ አመለጡ ?
ከመቐለ እስከ ኤርትራ ድንበር ድረስ ... 📍
በረጅም ጊዜ የትግል አጋሮቻቸው ታግተው የነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ አራት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር/እገታ አምልጠው ዛሬ መቐለ ገብተዋል።
ከእስር ካመለጡት አመራሮች አንዱ የሆኑት ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣኤ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ፣ የእገታቸውን ሂደት፣ የነበሩበትን ሁኔታ እና እንዴት ሊያመልጡ እንደቻሉ አጭር መረጃ ሰጥተዋል።
ኮሎኔል ተወልደ እንደገለጹት፣ እሳቸውን ጨምሮ የታገቱ አመራሮች ከመቐለ ይዘዋቸው የወጡት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች ወደ መቐለ በገቡበት ዕለት ነው።
በዕለቱ ሙሉ ሌሊት ሲጓዙ አድረው መጀመሪያ ወደ አክሱም እና ዓድዋ ከተሞች ተወስደዋል።
በወቅቱም ታጋቾቹ የተበታተኑ ሲሆን፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ እና አቶ ኢሳይያስ ታደሰ አክሱም ውስጥ፤ ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣኤ እና ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ ደግሞ ዓድዋ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ታስረው እንዲቆዩ ተደርጓል።
በዓድዋ አምስት ቀናት ከቆዩ በኋላም አመራሮቹ ወደ ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው ራማ ከተማ ተወስደዋል።
አመራሮቹ ታስረው የቆዩት በሆቴሎች እና በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሲሆን፣ ከቤተሰብም ሆነ ከማንኛውም አካል ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለው በጥብቅ ጥበቃ ሥር እንደነበሩ ኮሎኔል ተወልደ ገልጸዋል።
በዓድዋ በነበሩበት ወቅት አካላዊ ድብደባና ስድብ ባይኖርም አያያዙ ግን መጥፎ እንደነበር የገለጹት ኮሎኔሉ እሳቸው በቆዩበት ቤት ውስጥ ለ4 ቀናት ያህል ምንም ዓይነት ምግብ ሳይሰጣቸው እንደቆዩና ከ4 ቀን በኋላ በቀትር ወቅት ብቻ እንጀራ በሽሮ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል። ይህም ሆነ ተብሎ የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
በተጨማሪም ጥበቃ የሚያደርጉላቸው አካላት ልዩ ትዕዛዝ የተሰጣቸውና ሆነ ተብለው የተመረጡ በመሆናቸው ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር የማድረግ ፈቃድ እንዳልነበራቸው ገልጸዋል።
ለምን እንደታገቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮሎኔል ተወልደ ሲመልሱ፣ ምክንያቱ ሙሉ በሙሉ የሃሳብ ልዩነትና ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል።
በወቅቱ " የታገደው መንግሥታችን ይመለስ " እና " የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ይፍረስ " የሚሉ አካላት በነበሩበት ወቅት፣ እሳቸውና አብረዋቸው የታገቱት አመራሮች ግን " የፕሪቶሪያ ስምምነት ሊጣስ አይገባውም፤ 'መንግሥታችን ይመለስ' የሚለውን አንቀበልም፤ ይህም ወደ ሌላ ጦርነትና ዓለም አቀፍ መገለል የሚያስገባን በመሆኑ ትግራይ በአሁኑ ወቅት ሌላ ጦርነት የመሸከም አቅም የላትም፤ ሕዝቡም የሚፈልገው ሰላምና ምግብ ነው " የሚል ጽኑ አቋም በመያዛቸው፣ በአጋቾቻቸው ዘንድ እንደ "ፀረ-መከታችን" እና " ፀረ-ሥልጣናችን " ተቆጥረው እንደታገቱ አስረድተዋል።
ታጋቾቹን ለመፍታት የዲፕሎማሲ ጥረቶች እንደነበሩ የተጠየቁት ኮሎኔል ተወልደ፣ አጋቾቹ የውጭ ሀገራትንም ሆነ የዲፕሎማቶችን ተጽዕኖ የሚቀበሉና የሚሰሙ ሳይሆን ሥልጣናቸውንና ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያዩ በመሆናቸው የዲፕሎማሲ ጥረቱ ተጽዕኖ እንዳልፈጠረ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ታጋቾቹ ባሉበት ሁኔታ የትግራይ ፖሊስም ሆነ ፍርድ ቤት " ጉዳዩ አይመለከተኝም " ማለታቸውን አሳውቀዋል።
" የሚመለከተውን አካል ልናውቅ አልቻልንም፤ ማን ነው ወስኖ ያሰረን ? ማን ነው ከላይ የሚያዘው ? አናውቅም። ይነጋገሩ ነበር፤ ያወሩ ነበር፤ 'ለያዩአቸው' የሚል ትዕዛዝ ይወርድ ነበር፤ ማን ነው ግን እንደዚያ የሚያደርገው አናውቅም " ሲሉ አክለዋል።
" ለደህንነታቸው ብለን ነው የያዝናቸው " የሚለው ወሬም ከእውነት የራቀና በመሳሪያ ጥበቃ ሥር የተፈጸመ እገታ መሆኑን ገልጸዋል።
አመራሮቹ ወደ ራማ ከተማ ከተወሰዱ በኋላ 5 ቀን በሆቴል እና ስማቸውን መግለጽ ባልፈለጓቸው የአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት መታሰራቸውን አመልክተዋል።
በራማ የተሻለ አያያዝ ቢኖርም፣ የኤርትራ ድንበር ማረፊያ በሆነችው መረብ አካባቢ ሰዎች ሲሻገሩ በመመልከታቸውና መረጃዎችን በማደራጀታቸው፣ አጋቾቹ ወደ ኤርትራ ሊያሸግሯቸው እንደወሰኑና ሊለቋቸው እንደማይፈልጉ ማረጋገጣቸውን ኮሎኔል ተወልደ ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት አመራሮቹ " ከዚህ በላይ አልፈን መሄድ የለብንም፤ መውጣት አለብን " የሚል ውሳኔ በመወሰን፣ በሕይወት የመቆየት ተስፋቸው ዝቅተኛ ቢሆንም እና መስዋዕትነት ሊከፍሉ እንደሚችሉ ቢያውቁም፣ ብዙ ሰው የተሳተፈበትና ከፍተኛ ጥረት የተደረገበት እቅድ በማውጣት ከአጋቾቻቸው ፈቃድ ውጪ ማምለጥ ችለዋል።
" ተለቀው ነው " የሚባለው ውሸት መሆኑና በሌላ መንገድ እንዳመለጡ ነገር ግን አሁን ላይ በዝርዝር ለመናገር እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ኮሎኔል ተወልደ ከጓደኞቻቸው ጋር በሕይወት በመውጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ አጠቃላይ ክስተቱ የተጋሩን ክብርና ጀግንነት የሚያዋርድ፣ እንዲሁም የትግራይን ሕዝብ ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ እንደ ትግራዋይ ከፍተኛ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ትግርኛ መሆኑን ይገልጻል።
ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #mekelle📍 እነ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ መቐለ ገቡ። ለሁለት ሳምንታት በቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው ታግተው የቆዩት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የሚገኙባቸው 4 ከፍተኛ አመራሮች አሁን መቐለ መግባታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል። ወደ መቐለ ይዟቸው የገባው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው። መቐለ የገቡት ፦ 1. ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ 2. ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ…

8 hours ago