Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የቀድሞው የኮንጎ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ኤም23ን ያካተተ አዲስ ወታደራዊ ጥምረት መሰረቱ

ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የቀድሞው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ፣ በሩዋንዳ የሚደገፈውን ኤም23ን ጨምሮ የተለያዩ የታጠቁ ቡድኖችንና የፖለቲካ ሃይሎችን ያካተተ አዲስ ጥምረት መስርተዋል ።

ፕሬዝዳንቱ ጥምርቱን የመሰረቱት በሃገሪቱ ለዜጎች አዲስ ተስፋ ለማምጣት ነው ሲሉ ገልፀዋል። እርምጃው በሃገሪቱ ያለውን የፀጥታውን ሁኔታ አደጋ እንዳይጥል ስጋት ደቅኗል ።
ወታደራዊ ጥምረቱን ያቋቋሙት ካቢላ ባለፈው ዓመት በሀገር ክህደት እና በጦርነት ወንጀሎች ተከሰው በሌሉበት ሞት ተፈርዶባቸዋል ። በወቅቱ ፕሬዝዳንቱ ክሱን ውድቅ አድርገውታል።

ከ120 በላይ አማፂያን ቡድን በሚንቀሳቀስባት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለዜጎች ሞት፣አስገድዶ መደፈርና መፈናቀል ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል ።

በደረጀ መንግስቱ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.