Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
🔥 " በዛፍ ስር ተጠልለን ነው ያለነው፤ የዕለት ጉርስ እንኳ የለንም " - ተጎጂ አርሶ አደሮች

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፣  " ምስትንክር " በምትባል ጎጥ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም ረፋድ 3:30 አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ የ30 አባውራዎች 56 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

52 የሳር እና 4 የቆርቆሮ ቤቶች፣ 348 ኩንታል እህል፣ አልባሳት፣ የቤት እቃዎች፣ 8 የንብ ቀፎዎች እና ዶሮዎች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አርሶ አደሮች " የአደጋው መነሻ ምን እንደሆነ አናውቅም ፤ ከኩሽና ነው የተነሳው የሚል ወሬ ነው የሰማነው " ብለዋል።

" ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ስለሆነ ሁሉም ወደ ስራ ቦታ በሄደበት ወቅት ነው ቃጠሎው የተከሰተው " ሲሉ አስረድተዋል።

እሳቱ ከባድ እንደነበርና  ያዩ ሰዎች ለመቆጣጠር ቢሞክሩን እንዳልቻሉ፤ የ30 አባወራዎች አንድም ንብረት ሳይተርፍ ለዕለት ጉርስ የሚሆን ነገር ሳይቀር መውደሙን ገልጸዋል።

171 የህብረተሰብ ክፍሎች ለችግር የተጋለጡ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በእድሜ የገፉ ሽማግሌዎችና ህፃናት ናቸው።

የወረዳው አስተዳደር የመጠለያ ሸራ ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት የምግብ ድጋፍ አልተደረገላቸውም።

አርሶ አደሮቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት፣ ንብረታቸው በሙሉ በመውደሙ በዛፍ ስር ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ አጣዳፊና አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.