Logo
Tikvah-University
#monday_inspiration

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የባዮሜዲካል ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጽጌ ከተማ የ BRICS+ ሴቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ 2026 ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጽጌ በሕክምናና ባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው በዓለም ታዋቂ የሆነው ሽልማት አሸናፊ የሆኑት፡፡ 👏👏

ደከመኝ የማያውቁት ተመራማሪዋ፣ በመላው ዓለም ለሚገኙ ወጣትና ሴት ተመራማሪዎች ትልቅ ምሳሌ እንደሆኑ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው የደስታ መልዕክት ገልጿል፡፡

ሽልማቱ ተመራማሪዋ ለዓመታት ሳይሰለቹ ላከናወኑት ምርምር እና አበርክቶ እውቅና የሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ባዮሎጂ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር የሆኑት ጽጌ፣ ከ35 በላይ የምርምር ጽሑፎችን በግልና በጋራ ማሳትማቸው ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.