ወ/ሮ ለሊሴ ዱጋ ከስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን መሪነታቸውን አጠናቀቁ
#ethiopia | ለስድስት ዓመታት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ወይዘሮ ለሊሴ ዱጋ ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።
ወ/ሮ ለሊሴ በቆይታቸው በኢትዮጵያ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፉ ሲሆን በተለይም «ቪዚት ኦሮሚያ» የተሰኘውን የቱሪዝም ብራንድ ከምንም በመነሳት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙ ከፍ ብሎ እንዲጠራና ለሌሎች ክልሎችም አርአያ እንዲሆን አስችለዋል።
የኦሮሚያን የቱሪዝም ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት፣ የሥራ አጋርነትን የማጠናከር፣ ዲጂታል ቱሪዝምን የማሳደግ፣ «የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት»ን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የማሳደግ እንዲሁም ለኢንቨስትመንትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ አዳዲስ መንገዶችን የመክፈት አበይት አሻራዎችን አሳርፈዋል።
በተጨማሪም የሀገሪቱንና የክልሉን የተፈጥሮና የባህል መስህቦች ዓለም በሚረዳው ቋንቋና መንገድ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ኢንሼቲቭ በመቅረፅና በመተግበር ረገድ የጎላ ሚና ተጫውተዋል።
ኮሚሽነሯ በሥራ አፈጻጸማቸው፣ በትህትናቸውና ሰዎችን ለመርዳት ባላቸው ዝግጁነት የሚታወቁ ሲሆንበሥራ አጋጣሚያቸው ወቅት ያጋጠማቸውን የካንሰር ሕመም በጽናት ታግለው በማሸነፍ ለሌሎችም የጽናት ማሳያ ሆነዋል።
''የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት'' በተከበረበት ወቅት በለተቋሙና ለዘርፉ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦና አገልግሎት ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን በሚቀጥለው አዲስ የሕይወትና የሥራ ምዕራፋቸውም መልካም ሁሉ እንመኛለን።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

19 hours ago