Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የኢሚግሬሽን እና የ"ፋይዳ" ሲስተሞችን ለማስተሳሰር ንግግር ተጀመረ

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) አገልግሎቶቻቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስተሳሰርና የተቀናጀ አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችላቸውን ንግግር ጀምረዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በሁለቱ ተቋማት መካከል በሚከናወነው የሲስተም ትስስር ዙሪያ የጋራ ግምገማ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ይህ የተጀመረው የሲስተም ትስስር ንግግር ከግብ ሲደርስ ዜጎች ለፓስፖርትም ሆነ ለሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች በተደጋጋሚ የአሻራና የገጽታመረጃ መስጠት አያስፈልጋቸውም ተብሏል።

በውይይቱ ወቅት እንደተገለጸው ይህ የቴክኖሎጂ ውህደት ሀገሪቱ ለጀመረችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ሲሆን ተገልጋዮች የፋይዳ ስርአትን በመጠቀም ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
16 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.