Logo
SeledaPost
ዘመን ባንክ 10 ቢሊዮን ብር  የሚጠጋ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ባንኩ የአንድ አክሲዮን ትርፍ ድርሻ 53.9 በመቶ መድረሱን አስታውቋል።

ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ላይ እንዳስታወቀው፣ ከተመዘገበው ከታክስ በፊት ትርፍ ውስጥ 6.75 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘት ችሏል።

የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ ገቢ 17ነጥብ9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ አጠቃላይ ሀብቱም በ31ነጥብ3 በመቶ በማደግ 116 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

2018 በጀት ዓመት ለዘመን ባንክ ጠንካራ የፋይናንስ አፈጻጸምና ቀጣይነት ያለው እድገት የተመዘገበበት ዓመት ነበር ያሉ ሲሆን  የተመዘገበው ውጤት የባንኩን ጠንካራ የሥራ አፈፃፀም፣ የደንበኞችና ባለአክሲዮኖችን እምነት እንዲሁም የሠራተኞችን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልጸው፤ በቀጣይም በፈጠራና በደንበኛ ተኮር አገልግሎቶች እድገቱን ለማስቀጠል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ በበኩላቸው፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 14ነጥብ3 ቢሊዮን ብር፣ ጠቅላላ ካፒታሉ ደግሞ ወደ 26 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለተገኘው ስኬት ለሠራተኞች፣ ለደንበኞችና ለአጋሮች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በዘርፉ ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች ሲገመገም የዘመን ባንክ የፋይናንስ ውጤት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከሚታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞች መካከል አንዱ እንደሆነ ተመልክቷል።

Seledadotio
Seledadotio
20 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.