" ከኢትዮጵያ ጋር ላለን ጠንካራ ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ እንሰጣለን " - ጌዲዮን ሳር
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጌድዮን ሳር ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጹ።
ሚኒስትሩ ፤ የኢትዮጵያን አንድነትና ጸጥታ አስጠብቆ ማቆየት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው ሰላም ያለው ወሳኝ ሚና ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ሁለቱ አገራት የጋራ ፍላጎት እንዳላቸውና ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ጠንካራ ወዳጅነት ከፍተኛ ዋጋ የምትሰጥ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት፣ የሁለቱን አገራት ሁለገብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን በውይይቱ እንዳረጋገጠች አሳውቀዋል።
ይህ ውይይት የተደረገው የእስራኤል ጎረቤት ግብፅ የቀጠናው ሀገራት የሆኑትን የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን መሪዎች ሀገሯ ላይ ሰብስባ ስለ ቀይ ባህር፣ ስለ አባይ ወንዝ ፣ እስራኤል የሀገርነት እውቅና ስለሰጠቻት ሶማሌላንድ ስለሚሰጣት እውቅናና ድጋፍ ማውገዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክራ " የጋራ " ያለችውን መግለጫ ካወጣች ከ2 ቀን በኋላ ነው።
እስራኤል፣ ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በይፋ ወጥተው ከደገፉ እና ከኢትዮጵያ ጎን ነን ካሉ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #egypt በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጥሪ በግብፅ ኒው ኤል-አለሚን ከተማ የግብፅ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጎረቤታች የሆኑት የሱዳን ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የመሪዎች ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ስብሰባው ላይ የነበሩት ፦ - የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ - የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ (በግብፅ አውሮፕላን ተልኮላቸው ወደ ግብፅ የሄዱ) - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ…

1 day ago