(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤል ማዕከላዊ ምርጫ ኮሚቴ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወታደራዊ ሠፈርን ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅመዋል በሚል በድጋሚ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈባቸው። በተጨማሪም በግል ማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ የጫኑትን ተያያዥ የቪዲዮ መረጃ እንዲያጠፉ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እንዳስታወቁት፣ ኔታንያሁ 'ቴል ኖፍ' በተባለው የአየር ኃይል ሠፈር ውስጥ ወታደራዊ አውሮፕላንን ከጀርባቸው አድርገው የተቀረጹት ቪዲዮ "የምርጫ ቅስቀሳ" ሕግን የጣሰ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን እና የሕዝብን ሀብት (ወታደራዊ ሠፈርን ጨምሮ) ለግል የፖለቲካ ቅስቀሳ በመጠቀማቸው 2,500 ሰቅል እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን፣ ቪዲዮውን ከግል ገጻቸው ላይ እንዲያነሱ ታዘዋል። (በይፋዊ የመንግስት ገጻቸው ላይ ግን ማቆየት እንደሚችሉ ተገልጿል)።
በዚህ አወዛጋቢ ቪዲዮ ላይ ኔታንያሁ ከምርጫው በፊት በእስራኤል ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸውን ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። ኮሚቴው ከዚህ ቀደምም በደቡብ ሊባኖስ በሚገኝ የእስራኤል ወታደራዊ ይዞታ ውስጥ የተቀረጸ ሌላ ቪዲዮ በተመሳሳይ ለቅስቀሳ ውሏል በማለት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የ29,000 ሰቅል ቅጣት መጣሉ ይታወሳል።
በመጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በሚካሄደው የእስራኤል የፓርላማ ምርጫ፣ በኔታንያሁ የሚመራው 'ሊኩድ' ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቀዋል። የቅርብ ጊዜ የሕዝብ አስተያየት ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ሁለቱም ወገኖች መንግስት ለመመስረት የሚያስፈልገውን 61 ወንበር ለማግኘት በእጅጉ እየተፎካከሩ ሲሆን፣ የኔታንያሁ ጥምረት 51 እንዲሁም ተቃዋሚዎች 52 ወንበር ሊያገኙ እንደሚችሉ ተገምቷል።
በእስራኤል ታሪክ እጅግ የቀኝ አክራሪ (ወግ አጥባቂ) የተባለውን መንግስት እየመሩ ያሉት ኔታንያሁ፣ በአገር ውስጥ የሙስና ክስ እየተከታተላቸው ከመሆኑም ባሻገር፣ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤትም የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው አይዘነጋም።

9 hours ago