(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ሩሲያ ከፍተኛ ጥቃት ልትፈፅምብን እየተዘጋጀች ነው" ሲሉ ዘለንስኪ ገለፁ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ለመፈፀም በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታወቁ፡፡ ፕሬዝደንቱ ከመንግስት ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ አዛዦችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋር ዛሬ ባከናወኑት የስልክ ኮንፈረንስ ይህንን መግለፃቸውን ዩክሬንፎም ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው የሩሲያ ጥቃት መቼ እንደሆነና ምን አይነት መሳሪያዎችን እንደሚያካትት ይፋ ያላደረጉ ቢሆንም ከደህንነት አካላት ስለዝግጅቱ መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የሩሲያን ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ ዝግጅቶችን እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በሎጅስቲክስ በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት እያሟሉ መሆኑን መናገራቸውን የጠቀሰው ዘገባው ለመከላከያ ሚኒስትራቸውና ለአየር ሀይል አዛዡ ቁልፍ ተቋማትንና ንብረቶችን ለመጠበቅ ዝግጅት እንዲያደርጉ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን አስረድቷል፡፡ እንደዘገባው ዘለንስኪ ሲናገሩ ‹‹አስፈላጊው የኤፍ 16 ጥይቶች፣ ድኖን መጥለፊያና ፀረ ሚሳኤሎች አሉን፡፡ በጣም የሚያስቸግረው የባለስቲክ ሚሳኤል መከላከያ ነው፡፡ የዚህ አቅርቦት በአጋሮቻችን ላይ የተመሰረተ ስለሆነ እየተነጋገርን ነው›› ብለዋል፡፡

12 hours ago