Logo
SeledaPost
❗️የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጅ የሠጡ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎችን አደራጅቶ እያሠማራ መሆኑን ዋዜማ ከምንጮች ሠምታለች።

"የአማራ የሰላም ኃይል" በሚል ስያሜ በተደራጀው ኃይል ውስጥ በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ያልነበሩ ፈቃደኛ ግለሰቦችም ተካተዋል። ታጣቂዎቹ ራሳቸው በመረጡትና አካባቢያቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚደራጁ የገለጡት ምንጮች፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ለመንቀሳቀስ መስማማታቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

የጎንደር አካባቢ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎች ሥልጠና አጠናቅቀው ለግዳጅ የተሠማሩ ሲኾን፤ በተመሳሳይ በወሎ የፋኖ አባል የነበሩ ግለሰቦች የሚመሯቸው አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ መኾኑን ምንጮች ገልጸዋል።

ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈታረሙት የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ማስረሻ ሠጤ፣ አዲሱን አደረጃጀት በመፍጠር ሂደት ውስጥ እንዳሉበት ተረድተናል።

Seledadotio
Seledadotio
23 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.