Logo
EBC
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
*******************

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሁለተኛ የሥራ ዘመን በድጋሚ ለተመረጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጠው ይህ ታሪካዊ ውሳኔ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአመራርነት ጥበብና ለኢትዮጵያ ባላቸው ብሩህ ራዕይ ላይ የተጣለውን ታላቅ ህዝባዊ እምነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የዕድገትና የለውጥ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ኬንያ ምንጊዜም መልካም ምኞቷን እንደምትመኝ ያስታወቁት ፕሬዚዳንቱ፤ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ይበልጥ ለማስከበር፣ የቀጠናውን ሰላምና ዕድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረኮች በትብብር ለመስራት ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ወዳጅነት ይበልጥ አጠናክራ ለመቀጠል ሙሉ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በብሌን ደምበሎ
#ethiopia #kenya #pmabiyahmed #williamruto #hornofafrica

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.