(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሮይተርስ በዛሬ ዘገባው የኢትዮጵያ ፌዴራል ሀይሎችና አጋሮቹ መቀሌን ከተቆጣጠሩ በኋላም በትግራይ ክልል ውስጥ ግጭቱ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡ ሶስት እርዳታ ሰጪ ምንጮችን በምንጭነት የጠቀሰው ዘገባው በመቀሌ አካባቢ እንዲሁም በአድዋና በሽሬ ከተሞች ላይ የከባድ መሳሪያና የአየር ጥቃቶች መፈፀማቸውን ገልጿል፡፡ እነዚህ ጥቃቶች በሲቪሎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አስታውቆ በጠቅላላው 17 ሰዎች መገደላቸውን መስማቱን አስረድቷል፡፡ በቀጠለው ግጭት የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች የቴሌኮሚኒኬሽንና የመንቀሳቀስ ሁኔታው አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉንም ገልጿል፡፡
እንደዘገባው የመንግስት ሀይሎች ከመቀሌ በስተምእራብና በስተሰሜን ምስራቅ ወደሚገኙ አካባቢዎች እየገፉና ወደኤርትራ ድንበር እየተጠጉ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በተከዜ ወንዝ አቅራቢያ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ይህ ግጭት ወደኤርትራ ድንበር እየተቃረበ መሆኑ በተለይም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከተፈጠረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መበላሸት አኳያ ሰፊ ክልላዊ ውጥረትን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት እንዳለም ገልጿል፡፡ በተያያዘ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያና ኤርትራ ውጥረትን ከሚያባብሱና አለመረጋጋትን ከሚፈጥሩ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ መስጠቷን አውስቷል፡፡

2 days ago