የእንኳን ደስ አላችሁ እና የመልካም ምኞት መግለጫ!
*****
በአገራችን የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ የመንግሥት ምሥረታን ምክንያት በማድረግ ለመላው የአገራችን ሕዝቦችና ለአዲሱ መንግሥት እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ ለሰላማዊ የፖለታካ ሂደቶች ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን፤ ህዝባችን በአስከፊ የፀጥታ ስጋትና መዋከብ ውስጥ ሆኖም ስልጣን የሚፀናው በድምፄ ብቻ ነው በሚል ቁርጠኝነት በነቂስ ወጥቶ ምርጫ በማድረግ ከምርጫ ውጪ ላሉ የስልጣን ፍላጎቶች ግልፅ መልእክቱን አስተላልፏል።
በመሆኑም በዚህ የላቀ ህዝባዊ ቁርጠኝነት በታየበት ምርጫ የተመሠረተው መንግሥት አገራችንን ወደ ተሻለ ሁለንተናዊ የዕድገት እና ሰላም የሚያሸጋግር፤ የሕዝባችንን ጥያቄዎችና እውነተኛ ፍላጎቶች የሚመልስ እንዲሆን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምኞቱን ይገልጻል።
ዛሬ ለተሾሙት የመንግሥት አመራሮች በሙሉ የተጣለባችሁን ታሪካዊና አገራዊ ኃላፊነት በታማኝነት፣ በፍትሐዊነትና በትጋት በመወጣት አገራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የምታደርጉት ጉዞ የስኬትና የድል እንዲሆንላችሁ አብን እየተመኘ፤ በሰባተኛ ዙር አንደኛ መደበኛ መስራች ጉባኤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሜ የተመረጡትን ክቡር ዐብይ አሕመድን (ዶ.ር) ፓርቲያችን አብን እንኳን ደስ አለዎት ማለት ይወዳል።
አገራችን ያለችበትን ሁለንተናዊ ነባራዊ ሁኔታ፣ ያጋጠሙንን አገራዊና ቀጣናዊ ተፎካካሪ ሁኔታዎች እንዲሁም የሕዝባችንን የልማትና የፍትህ ጥያቄዎች በተገቢው በመረዳት አገራችንን ወደ ተሻለ የዕድገትና የሰላም ምዕራፍ ይመራሉ ብለን እናምናለን። በመሆኑም ድርጅታችን አብን፤ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት እንዲሁም የሕዝባችንን የኑሮ ውድነት የሚያቃልሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ለመተግበር በሚወሰዱ ሀገራዊ እርምጃወች በትብብር ለመሥራት ዝግጁነቱን ያረጋግጣል።
በመጨረሻ ድርጅታችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሀገራዊ ጥቅም፣ አንድነትና ህልውና በሚጠይቀው ቦታ ሁሉ ጽኑ አጋርነታችንን እየገለጽን፣ ፍትሕና እውነት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ድምፅ ሆነን መቆማችንን እንቀጥላለን። በድጋሜ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና ለአዲሱ መንግስታቸው ስኬትን እንመኛለን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
መስከረም 25/2019 ዓ.ም

10 hours ago