Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የግብፅ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያ እና የሱዳን መሪዎች በግብፇ ኤል-አላሜይን ከተማ ያልተጠበቀ የአራትዮሽ ጉባኤ አካሂደዋል። መሪዎቹ በቀጠናው እየተባባሰ ለመጣው ግጭት፣ በተለይም በሱዳን እና በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚያገረሸው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ ቢያቀርቡም፤ ከስብሰባው በኋላ ያወጡት የጋራ መግለጫ ግን በቀጥታ የኢትዮጵያን ብሔራዊ የውጭ ፖሊሲዎች የሚሞግት ሆኖ ተገኝቷል።

የጋራ መግለጫው "የቀይ ባህር አስተዳደር የባህር ዳርቻ ሀገራት ብቻ መብት ነው" በማለት የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት በግልፅ ሲቃወም፤ በናይል ወንዝ ላይ "የአንድ-ወገን እርምጃ የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ይጎዳል" በማለት የታላቁን ህዳሴ ግድብን አጀንዳ በድጋሚ ኮንኗል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ ዳግም አገርሽቶ የፌደራል መንግስት ኃይሎች የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌን ዳግም መቆጣጠራቸው ተዘግቧል። አዲስ አበባ ጎረቤቶቿን (ግብፅ፣ ሱዳን እና ኤርትራን) አማፂያንን በመደገፍ ብትከስምም፣ ሶስቱም ሀገራት ክሱን አስተባብለዋል። ይባስ ብሎ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር፣ "ኢትዮጵያ ኤርትራን ለማጥቃት የውሸት ሰበብ እየፈለገች ነው" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ከባድ ክስ ሰንዝረዋል።

የፖለቲካ ተንታኞች ይህንን ክስተት ሲያብራሩ፣ ግብፅ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጎረቤቶች በአንድ በማሰባሰብ ጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ እና የደህንነት ከበባ እየፈጠረች መሆኑን ያሳያል ይላሉ። ኢትዮጵያ በአንድ ጊዜ ከምስራቅ በሶማሊያ፣ ከምዕራብ በሱዳን፣ እና ከሰሜን በኤርትራ በኩል በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቃለች። አዲስ አበባ የውስጥ ጦርነቷን በአጭሩ ቋጭታ ይህንን የተናበበ የውጭ ጥምረት መቋቋም ካልቻለች፣ የቀንድ አፍሪካ ጂኦ-ፖለቲካ ወደ ባሰ የደህንነት ስጋት ሊያመራ እንደሚችል ተገምቷል።
_____
🗣️ ውድ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች... እናንተስ ምን ታስባላችሁ?
ይህ አዲሱ በግብፅ አቀናባሪነት የተመሰረተው የአራቱ ሀገራት ጥምረት በኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ያመጣል? የውስጥ አንድነታችንንስ ለማስጠበቅ ምን መደረግ አለበት? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን!

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.