Logo
FBC
የመንግሥት የመፈጸም አቅም የተገለጸበት የስንዴ አብዮት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷን ለማሟላት እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ድረስ የውጭ ምንዛሪ ታወጣ ነበር።

ይህ የሚሆነው ደግሞ መሬት፣ ውሃ እና ማልማት የሚችል ከፍተኛ የሰው ኃይል ይዛ መሆኑ እጅግ ያስቆጫል። በዚህ የቁጭት መንፈስ ወደ ስራ የገባው የመደመር መንግሥት ፀጋን በመለየት፣ የፖሊሲ ርምጃ በመውሰድ እና በቆራጥ አመራር ታሪክን የቀየረ ውጤት አስመዝግቧል።

ያለውን ፀጋ በመጠቀም ግብርናውን ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ የላቀ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በተለይ በስንዴ ሰብል ላይ የተመዘገበው ስኬት አስደማሚ ነው።

ውጤቱ ኢትዮጰያን በስንዴ አምራችነት ከአፍሪካ አህጉር ቀዳሚ ሲያደርጋት፤ ለስንዴ ግዢ ይወጣ የነበረውን እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ከማስቀረት ባለፈ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማምጣት አስችሏል።

የመደመር መንግሥት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በስፋት በመተግበር፣ አሲዳማ መሬቶችን በኖራ በማከም እና ረግረጋማ ቦታዎችን በቴክኖሎጂ በማጠንፈፍ ታሪካዊ ለውጥ አምጥቷል።

በኩታ ገጠም እርሻና በዘመናዊ ማሽነሪዎች አጠቃቀም የታጀበው የልማት ጉዞ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያን ስንዴ የማምረት ዓቅም 33 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን አድርሷል።

በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ዘርፍ ትልቅ እመርታ አሳይቷል፤ የመደመር መንግሥት የመስኖ ልማት፣ ሜካናይዜሽን፣ የግብዓት አቅርቦት እና የግብርና ኤክስቴንሽን ድጋፍ በማጠናከሩ ከፍተኛ ምርት ሊገኝ ችሏል።

የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት ከ290 እስከ 340 ሚሊዮን ኩንታል (ከ29 እስከ 34 ሚሊዮን ቶን) በላይ መድረሱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉር ቀዳሚ የስንዴ አምራች ሀገር አድርጓታል።

የስንዴ ልማቱ አርሶ አደሩን ከቀድሞው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ አላቅቆ፣ በኩታ ገጠም እርሻና በሜካናይዜሽን ታግዞ ወደ ሰፋፊ የንግድ ምርት እንዲገባ መንገድ ጠርጓል።

የተሻሻሉ የስንዴ ሰብል ዝርያዎች መለቀቃቸው ለዚህ ውጤት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፤ የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን ማዘመን በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ነው።

በምርት አቅም እና በኩታ ገጠም እርሻ የተመዘገቡት እነዚህ ሰፊ ስኬቶች፣ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ አቅም እያደረገችው ያለውን ሁለገብ ማንሰራራት በግልጽ ከማሳየት ባለፈ፤ የመንግሥትን የመፈጸም ዓቅም የሚያሳይ ተምሳሌታዊ ስራ ነው።

ይህ ትልቅ ለውጥ ኢትዮጵያ ከድህነትና ከዕርዳታ ጥገኝነት ወጥታ የምግብ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራትም ተስፋ የሚሰጥ አህጉራዊ አርዓያ መሆን መቻሏን አስመስክሯል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.