Logo
YenetaTube
በተለያዩ አካባቢዎች የሚጠየቀው የአሽከርካሪዎች የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱ ተገለጸ

👉በ2019 የኮቴ ክፍያን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይሰራል ተብሏል

በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና በፌደሬሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር በተከናወነ ሥራ አሽከርካሪዎች የሚጠየቁት አግባብነት የሌለው የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን አስታውቋል።

የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፤ ክፍያው በሀገሪቱ ሕግ የማይፈቀድ በመሆኑ ከክልሎች ጋር በተደረገ ውይይት እንዲቀንስ ተደርጓል።

በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በጂቡቲ ኮሪደር የሚጠየቀው ክፍያ መቀነሱን ተናግረዋል።

የኮቴ ክፍያ አሁንም ባልቀረባቸው አካባቢዎች በ2019 የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት መንግሥት እና ፌደሬሽኑ በትኩረት እንደሚሠሩ አቶ ብርሃኔ ዘሩ ገልጸዋል።

በህይወቴ ጌትነት

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.