ላለፉት 10 ቀናት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን የከተማይቱ አራት ነዋሪዎች ተናገሩ።
አገልግሎቱ ወደ ነበረበት የተመለሰው ዛሬ እሁድ መስከረም 24፤ 2019 ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች መንግስታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ይሰጣቸው የነበሩት የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡት ሐሙስ መስከረም 14 ምሽት ላይ ነበር። ሌላኛው የቴሌኮም አገልግሎቶች ሰጪ ድርጅት የሆነው የሳፋሪኮም ኔትወርክ ግን እስከ አርብ እኩለ ቀን ድረስ ሲሰራ ቆይቶ ተቋርጧል።
የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳፋሪኮም የኢንተርኔት እና የስልክ “ኔትወርኮቻቸውን እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ” የሰጠው፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጭን ጨምሮ ስለጉዳዩ የሚያውቁ አራት ግለሰቦች እንደነገሩት “ሮይተርስ” በወቅቱ ዘግቦ ነበር። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዛሬ እሁድ ያነጋገረቻቸው የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፤ በቀጥታ ስልክ መደወል እንደቻሉ የኢንተርኔት አገልግሎትም እየተጠቀሙ መሆኑን ተናግረዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube FikerAssefa

4 days ago