ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያን ጨምሮ 81 መሰረታዊ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግስት አስረከበ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ እና አዲስ ፖሊሲ የሚፈልጉ 81 መሰረታዊ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግስት ማስረከቡን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ በአጠቃላይ 394 ምክረ ሐሳቦችን አዘጋጅቶ ማስረከቡን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አጀንዳዎቹን ለክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እንዲሁም ለአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች አስረክበዋል።
የትግራይ ክልልን አጀንዳ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር በይፋ ተረክበዋል። የፌደራል መንግስትን የተመለከተውን አጀንዳ ከምክረ ሐሳብ ጋር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተረክበዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን የቀረቡት ምክረ ሐሳቦች ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል። ዋና ኮሚሽነሩ በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሰረት ትግበራዊ ክትትል እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል።
በተለይም አዲስ የሚቋቋመው መንግስት በዚህ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠው የሦስት ዓመት የሥራ ዘመን የነበረ ቢሆንም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሁለት ጊዜ ተራዝሞለታል። በዚሁ መሰረት በየካቲት 2017 ዓ.ም ለአንድ ዓመት እንዲሁም በየካቲት 2018 ዓ.ም ለተጨማሪ ስምንት ወራት መራዘሙ ይታወሳል። የኮሚሽኑ የተራዘመ የሥራ ዘመን በያዝነው የ2019 ዓ.ም. ጥቅምት ወር በይፋ ያበቃል።
አሐዱ_ሬዲዮ

2 days ago