(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፌደራል መንግስት መቀሌን መቆጣጠሩን ተከትሎ የትግራይ ኃይሎች ወደ ኤርትራ ድንበር እያፈገፈጉ መሆናቸውንና ይህም ጦርነቱን ወደ አዲስ እና አደገኛ የቀጥታ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ሊያሸጋግረው እንደሚችል አቶ ጃዋር መሐመድ ባወጡት አዲስ የፖለቲካ ትንታኔ አስጠነቀቁ።
አቶ ጃዋር ባወጡት ሰፊ ትንታኔ እንዳብራሩት የህወሓት አመራሮች እና የዕዝ ሰንሰለቱ ከመደበኛ የከተማ ውጊያ ወደ ተንቀሳቃሽ (ደፈጣ) ውጊያ ለመሸጋገር በማሰብ ወደ ኤርትራ ድንበር አካባቢ ማፈግፈጋቸውን ጠቁመዋል። ይህ የህወሓት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በተቋረጠበት በአሁኑ ወቅት የሁለቱን አገራት መሪዎች ከባድ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ፈተና ውስጥ እንደከተታቸው ትንታኔው ያብራራል።
በጥናቱ መሰረት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለት የተጣረሱ ምርጫዎች ተደቅነውባቸዋል። አንደኛው የህወሓት ኃይሎች ወደ ግዛታቸው ገብተው እንዲደራጁ መፍቀድ ሲሆን፣ ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚፈልጉትን የተኪ ጦርነት (Proxy war) ግፊት ለማስቀጠል ይረዳቸዋል። ይሁን እንጂ ይህን ማድረጋቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድንበር ጥሰው ወደ ኤርትራ እንዲገቡ ህጋዊ እና የደህንነት ሽፋን ሊሰጣቸው ስለሚችል አስመራን በቀጥታ ወደ ጦርነት ያስገባታል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግስትም ከባድ የውሳኔ ማዕበል ውስጥ እንደሚገኝ አቶ ጃዋር ጠቁመዋል። የፌደራል መንግስቱ የህወሓት ኃይሎች ጊዜ አግኝተው ዳግም እንዳይደራጁ ድንበር ጥሶ ፈጣን እርምጃ መውሰድን ከመረጠ፣ ከኤርትራ መደበኛ ጦር ጋር በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ከመግባቱም በላይ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ሊያስቆጣ ይችላል።
በአንፃሩ እርምጃ ሳይወስድ መጠበቁ፣ ህወሓት ጊዜ አግኝቶ ከውጭ አጋሮቹ (በተለይም በድንበር እና በጂኦ-ፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ ካሉት ሱዳን እና ግብፅ) ጋር በመቀናጀት ይበልጥ አደገኛ ሀይል ሆኖ እንዲወጣ እድል ሊሰጠው እንደሚችል ተንትነዋል።
ሲያጠቃልልም አቶ ጃዋር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ ክፍለ ጦሮችን እና ተንቀሳቃሽ ድልድዮችን ወደ ሰሜን ዕዝ እያንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመው፤ አስቸኳይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ተፈልጎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ካልመጡ በቀር፣ ግጭቱ የትግራይን ድንበር አልፎ ወደ ኤርትራ ግዛት የሚሸጋገርበት እጅግ አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አጽንኦት ሰጥተዋል።

3 days ago