Logo
AHADU RADIO FM 94.3
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ25 ኤምባሲዎች ባሉበት ሆነው የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱ ተገለጸ

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በ25 ኤምባሲዎች በኩል ሥራ መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።

ተገልጋዮች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ ለአሐዱ ሬድዮ ገልጸዋል።

ተቋሙ አገልግሎቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹን ቁጥር ከ38 ወደ 40 ማሳደጉ ተገልጿል።

ከነባር ቅርንጫፎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ አጣና ተራ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች ተጨማሪ የፓስፖርት ቅርንጫፎች ተከፍተዋል።

በተያዘው የበጀት ዓመት በሁሉም የአንድ መሶብ ማዕከላት የፓስፖርት አሰጣጥ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ አምቦ መቃሳ ተናግረዋል።

በህይወቴ ጌትነት

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.