Logo
SeledaPost
የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ሠራዊት መቀሌ ከተማ መግባታቸው ተገለፀ

​የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ሠራዊት መቀሌ ከተማ መግባታቸውን ተከትሎ፣ ከዛሬ ሌሊት 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የህወሓት ሠራዊት ከመቐለ ከተማ በሁሉም አቅጣጫዎች እየወጣ ይገኛል ተብሏል።

​የከተማዋ ቁጥጥርና የሰራዊት እንቅስቃሴ፦ የመከላከያ ሠራዊቱ እና የትግራይ ሰላም ሠራዊት መቀሌ ከተማ መግባታቸውን ተከትሎ የህወሓት ሠራዊት አባላት ከመቐለ ከተማ እየወጡ ይገኛሉ።

​የመውጫ መስመሮች እና ቁጥጥር፦ የህወሓት ሠራዊት በዋናነት የመቐለ - ሓውዜን - ዕዳጋዓርቢ መስመሮችን እየተጠቀመ እንደሚገኝ እና ማንኛውም አመራር እንዳይቀር በተደረገ ጥብቅ ሰው በሰው ቁጥጥር እንቅስቃሴው እየተመራ እንደሆነ ተመላክቷል።

​በሌሎች ከተሞች የሚታይ እንቅስቃሴ፦ የዚሁ እንቅስቃሴ አካል በሆኑት የዓድዋ፣ አክሱም እና ራማ ከተሞች በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሰው ስብስብና ጥልቅ እንቅስቃሴ እንደሚታይ ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Seledadotio
Seledadotio
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.