Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#addisababa

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተጠናቀቀ።

የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ " በዓሉ ባህላዊ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ፣ በሰላም፣ በደስታና በልዩ ድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል " ብለዋል።

" ኢሬቻ የምስጋና ፣ የሰላም ፣ የፍቅርና የአንድነት ሕያው መገለጫ ነው " ያሉት ከንቲባዋ " ከባህላዊ እሴቱ ባሻገር፣ የተለያዩ ሕዝቦች በፍቅርና በወንድማማችነት የሚገናኙበት፣ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቻችን የሚጎሉበት ታላቅ በዓል ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በዓሉ በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ሁሉ፣ በተለይ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በፍቅር ላስተናገዱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፣ አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች ፣ ፎሌዎች ፣ የጸጥታ አካላትንና አመራሮች በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia Photo
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.