Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ የድሬድዋ ከተማ ከንቲባ ማናቸው ?

የድሬዳዋ ከተማ ም/ ቤት አቶ አብዱላሂ አደምን የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ ሾሟል። ለመሆኑ አዲሱ ከንቲባ ማናቸው ? ስለ ትምህርትና የስራ ጉዟቸውስ ምን ይታወቃል ?

በኤረር ከተማ ተወልደው ያደጉት አቶ አብዱላሂ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው ኤረር እና በአዲስ አበባ አጠናቀዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሺዮሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። የማስተርስ ዲግሪያቸውን በቻይና በዓለምአቀፍ ግንኙነት መስክ አጠናቀዋል።

በስራ ዓለም ፦
-  ከ2001 እስከ 2003 ዓ.ም. የኤረር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የኤረር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ፣
- ከ2004 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ፣
- ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሶማሊ ክልል በአደጋ ሥጋት ቢሮ፣ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ በግብርና ቢሮና በትምህርት ቢሮ በአመራርነት ሰርተዋል።

ከንቲባ እስከሆኑበት እስከዛሬው ቀን ድረስ የሶማሊ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

የአማርኛ ፣ አፍ ሶማሊና የአፋን ኦሮሞ እንዲሁም የእንግሊዘኛ ቋንቋንዎችን አቀላጥፈው ይናገራሉ ተብሏል።

መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሀርን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። ምክትል ከንቲባው በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። አቶ ከድር ጁሀር ላለፉት ዓመታት ከተማዋን ከንቲባ ሆነው ሲመሩ ቆይተው በዛሬው ዕለት በአቶ አብዱላሂ አደን ተተክተዋል። መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.