በዩኔስኮ ለመመዝገብ በሂደት ላይ የሚገኘውን የኢሬቻ በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚከበረውንና በዩኔስኮ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት ለመመዝገብ በሂደት ላይ የሚገኘውን የኢሬቻ በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ለአሐዱ እንዳስታወቀው፣ በዓሉን ለማስተዋወቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ዓለሙ ጌታሁን እንዳስታወቁት፣ ኢሬቻ የዴሞክራሲ ሥርዓትን የሚያሳይና የኦሮሞ ሕዝብ ከአባ ገዳ ሥርዓት ጋር አያይዞ ሲያከብረው የቆየ ነው።
በዓሉ የሥልጣን ሽግግርን በሰላማዊ መንገድ የሚያካሂድ በመሆኑ ከፍተኛ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
በቀጣይ በዓሉ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደሚከበር አቶ ዓለሙ ጠቁመዋል።
ኢሬቻን ጨምሮ ሌሎች ክልላዊ እና ብሔራዊ በዓላትን ሕብረተሰቡ በአንድነት ሊያከብራቸው እንደሚገባም አሳስበዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

6 days ago